‎በጎፋ ዞን የጋልማ ከተማ አስተዳደር ሕዝብ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ

‎በጎፋ ዞን የጋልማ ከተማ አስተዳደር ሕዝብ ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን አካሄደ

‎የሕዝብ ምክር ቤቱ በ4ኛ ዙር መርሃ-ግብር 12ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤው ለ2018 በጀት ዓመት ከ145 ሚሊዮን 930 ሺህ ብር በላይ በጀት አጽድቋል።

በጉባኤው ‎የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጋልማ ከተማ አስተዳደር ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ ዶርባ ዶቦ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ምክር ቤቶች የሕዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤት መገለጫ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በመንግስት አሠራር የሕዝብ ተሳትፎ ቀጥታ የሚረጋገጥባቸው ተቋማት መሆናቸውን ገልጸዋል።

‎ምክር ቤቱ በሕገ-መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን በመጠቀም የሕዝቡ የመልካም አስተዳደርና ሰላም የሚረጋገጥበት የመንግስት ሀብትና ንብረት ለታለመው አላማ እንዲውል በማድረግ የህዝብ ተጠቃሚነት ላይ በመከታተልና በመቆጣጠር የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ እየተጋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

‎በጉባኤው የ2018 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ እንዲሁም ልዩ ልዩ አጀንዳዎች በከተማው ምክትል አፈ ጉባኤ ወ/ሮ አልማዝ አለየ ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።

የከተማው ከንቲባ አቶ ያዕቆብ ዘካርያስ፤ ምክር ቤቱ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የከተማውን አቅም በማሳደግ ገቢን አሟጦ በመሰብሰብ በግብርናው ዘርፍ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በመሸጋገርና የወጣቶችን ተጠቃሚነት፣ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና ለህብረተሰቡ ተጠቃሚነት በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ለምክር ቤቱ አቅርበው በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡

‎ምክር ቤቱ በቆይታው ለ2018 የበጀት ዓመት 145 ሚሊዮን 930 ሺህ 148 ብር በጀት በማጽደቅና በሌሎች አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይቶ አቅጣጫዎችን አሰቀምጧል፡፡

‎የምክር ቤቱ አባላት በቀረበው በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ዙሪያ ሀሳብና አሰተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡

‎ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን