የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ ፈጣንና ቀልጣፉ አገልግሎት በመስጠት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ከግብ ማድረስ እንደሚገባ ተገለጸ

የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ ፈጣንና ቀልጣፉ አገልግሎት በመስጠት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ከግብ ማድረስ እንደሚገባ ተገለጸ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በጌዴኦ ዞን የገደብ ከተማ አስተዳደር ሲቪል ሰርቫንት በሰጡት አስተያየት የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ ፈጣንና ቀልጣፉ አገልግሎት በመስጠት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ከግብ ማድረስ እንደሚገባ ተናገሩ።‎

‎የከተማ አስተዳደሩ ፐብሊክ ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ ተቋማት፣ ለዳይሬክተሮች እና ባለሙያዎች የዕውቅና ሽልማት መርሃግብር አካሂዷል።‎

‎በመረሃ ግብሩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የጌዴኦ ዞን የሳይስና ኢንፎርመሽን ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ደረጀ ሾንጣ የተሻለ አፈፃፀም በማሳየት የተገልጋይን እርካታ ለማሳደግ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ተቋማትና ሲቪል ሰርቫንት ዕውቅና መስጠቱ የፓርቲያችን መርህ በመሆኑ በቀጣይም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል።‎

‎በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የገደብ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የከተማው ማዘጋጃ ቤታዊ አገልግሎት ሥራ አስኪያጅ አቶ ከተማ ሞጎስ በበኩላቸው የአገልግሎት አሰጣጣችንን በማዘመን የማህበረሰባችንን እርካታ ማሳደግ መቻል አለብን ያሉ ሲሆን ይህን ጅምር ለውጦች በቀጣይም በትኩረት አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።‎

‎አክለውም በ2017 በጀት ዓመት በአገልግሎት አሰጣጥ በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ በጥንካሬና በትኩረት ተግባራትን በመምራትና በመተግበር የታዩ ለውጦችን በማጎልበት በቀጣይ በ2018 ዓ.ም ይበልጥ አጠናክረን በማስቀጠል በተለይም የታዩ ጉድለቶችን መፍታት አለብን ብለዋል።‎

‎በገደብ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቨስ እና ሰው ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አስራት ማሞ በበጀት ዓመቱ በየተቋሙ ያሉ ሲቪል ሰርቫንት ተግባሮቻቸውን ከመወጣት ረገድ የተሻለ ለውጥ መታየቱን ገልጸው በቀጣይ ለማህበረሰባችን የዘመነ አገልግሎት መስጠት ላይ ትኩረት ልሰጥ ይገባል ብለዋል።‎

‎በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት አፈፃፃም ሪፖርት በኃላፊው የቀረበ ሲሆን፣ በሪፖርታቸው የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ የተለያዩ ስኬቶችም ቢስተዋሉም አንዳንድ የአሠራርና የመምሪያ ግድፈቶች፣ የፎርጀሪ ልየታ፣ ህገ ወጥ የደረጃ ዕድገት መሰጠት፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በመለየትና ከአሠራር ውጭ ክፍያ የተፈፀመ ከ500 ሺህ ብር በላይ ወደ መንግስት ካዝና ገቢ በማድረግ አስተዳደራዊ የእርምት እርምጃ በመውሰድ ለማረም መቻሉን ኃላፊው የገለፁት።‎

‎በመድረኩ የተሻለ አፈፃፀም በማስመዝገብ የዕውቅና ሽልማት ካገኙት መካከል አቶ አሸናፊ አሰፋ፣ ግዛው ጀቦ እና ሌሎችም ለማህበረሰባችን በቅንነት ማገልገል እና ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት ተገቢ በመሆኑ ያገኙት ውጤት እንዳስደሰታቸውና በቀጣይም ይበልጥ አጠናከረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።‎

‎በመድረኩ የዞን አመራርና ባለሙያ እንዲሁም የከተማው አስተባባሪ አካላትና የሲቪል ሰርቫንት ባለሙያዎች በመድረኩ ታድመዋል።‎

‎ዘጋቢ: ጽጌ ደምሴ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን