በሁሉም የትምህርት ስራዎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊንቀሳቀሱ ይገባል ሲል የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር አሳሰበ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 30/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በዞኑ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም የትምህርት ስራዎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊንቀሳቀሱ ይገባል ሲል የቤንች ሸኮ ዞን አስተዳደር አሳስቧል፡፡
የዞኑ ትምህርት መምሪያ “የጋራ እርብርብ ለላቀ የትምህርት ጥራት” በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ/ም የትምህርት ሥራዎች ንቅናቄ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የቤንች ሸኮ ዞን ምክትል አስተዳዳሪና የዞኑ ከተማ ልማት መምሪያ ሃላፊ አቶ መስፍን መንገሻ እንደተናገሩት ትምህርት ለአንድ ሀገር ዘላቂነት ያለው ዕድገትና ልማት ለማስመዝገብ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በዞኑ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በሁሉም የትምህርት ስራዎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ባለድርሻ አካላት በቁርጠኝነት ሊንቀሳቀሱ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
በተለይ በትምህርት ዘመኑ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስራዎችን በተደራጀ መልኩ መስራት እንደሚገባም መክረዋል።
የዞኑ ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ አገኘሁ ወርቁ እንደገለፁት ዛሬ በአለማችን ያደጉና በስልጣኔ ማማ የሚገኙ ሀገራቶች ዋነኛው ሚስጥር ለትምህርት በሰጡት ትኩረት ነው ብለዋል።
በተለይ የትምህርት ስራ የባለድርሻ አካላት ቅንጅትና ተሳትፎ የሚጠይቅ በመሆኑ በየደረጃው የሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት የነቃ ተሳትፎ ሊያደርጉ እንደሚገባም ጠቁመዋል።
የ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመኑን ስኬታማ ለማድረግ ከባለፈው የትምህርት ዘመን የነበሩ ድክመቶችን አርመን ጥንካሬን አጎልብተን ማስቀጠል ይገባናል ብለዋል።
በመድረኩ ላይ በመምሪያው የትምህርት ቤቶች ማሻሻል ዳይሬክቶሬት ቡድን መሪ አቶ ጌታሁን ቢኒያም የበጀት አመቱን ዕቅድ አፈጻጸም በተመለከተ በዝርዝር ሪፖርት አቅርበዋል።
በመድረኩ ላይ ከክልል ከዞንና ከወረዳ የተውጣጡ አመራሮች የትምህርት ዘርፍ ባለድርሻ አካላት ተሳታፊዎች ሆነዋል
ዘጋቢ፡ ጦያር ይማም – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
ለዜጎች ሰላምና ለሀገር ዕድገት የጸጥታዉ ዘርፍ ያለው ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ
የተገልጋይ እርካታን ለማሳደግ ፈጣንና ቀልጣፉ አገልግሎት በመስጠት የልማትና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን ከግብ ማድረስ እንደሚገባ ተገለጸ
የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ውይይት አካሄደ