‎የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ውይይት አካሄደ

‎የጌዴኦ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት የሥራ አፈጻጸም ውይይት አካሄደ

‎በ2017 በጀት ዓመት ውስን የመንግስት ሀብት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ተደርጓል ያሉት የጌዴኦ ዞን ፋይናስ መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማ ጤካሞ በአዲሱ በጀት ዓመትም ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠል የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት÷ አገልግሎት አሰጣጡን ዘመናዊና ቀልጣፋ ማድረግና የመንግስት ሀብት ለታለመለት ዓላማ እንዲውል ማድረግ የዕቅድ አካል ተደርጎ እንደሚሠራ ተናግረዋል።

የዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ በየነ ገደቾ በ2018 በጀት ዓመት በዞኑ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶች አንዲጠናቀቁ፣ በታችኛው መዋቅር ከግዢ ወቅታዊነት ጋር የሚታዩ ችግሮችን በመቅረፍ፣ የባከኑ ሀብቶችን በማስመለስ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ለተሻለ አፈጻጸም እንደሚሠሩ ጠቁመዋል።

‎በመርሃግብሩ በጡረታ የተሰናበቱ የመምሪያው ሰራተኞች ምስጋናና ሽኝት የተደረገላቸው ሲሆን በወናጎ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላና የቱቲቲ ትክል ድንጋይ ጉብኘት አድርገዋል።

‎ዘጋቢ: ውብሸት ካሣሁን – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን