የካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው

የካፋ ዞን ፖሊስ መምሪያ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ ነው

መድረኩ በመምሪያው የስራ አፈፃፀም ላይ በመወያየት የተሻሉ ልምዶችን ለማጎልበትና ጉድለቶችን ለማረም የሚያስችል ሀሳብና አቅጣጫ የሚመላከትበት ነው ተብሏል።

በ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ምክክር ተደርጎ የሚጸድቅ ሲሆን በተጠናቀቀው በጀት ዓመት የተሻለ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች የእውቅና መርሐ-ግብር እንደሚከናወን ከወጣው ፕሮግራም መረዳት ተችሏል።

በመድረኩ ባለፈው በጀት ዓመት የተከናወኑ አበይት ተግባራትን የሚያስቃኝ የፎቶ ኤግዝቢሽን ተዘጋጅቷል።

በውይይት መድረኩ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል፣ የካፋ ዞን፣ የወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፡ አሳምነው አትርሳው – ከቦንጋ ጣቢያችን