በጎፋ ዞን የደምባ ጎፋ ወረዳ ሕዝብ ምክር ቤት 4ኛ ዙር 3ኛ መደበኛ ጉባኤ እየተካሄደ ነው
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደምባ ጎፋ ወረዳ ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈጉባኤ አቶ አበበ አማኔ ባስተላለፉት መልዕክት ምክር ቤቶች የሕዝብ ሉአላዊ የስልጣን ባለቤት መገለጫ በዲሞክራሲ ስርዓት ግንባታና በመንግስት አሠራር የሕዝብ ተሳትፎ የሚረጋገጥባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
ምክር ቤቱ በሕገ-መንግስቱ የተሰጠውን ስልጣን በመጠቀም የሕዝቡን የመልካም አሰተዳደር እና የወጣቶች ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በመከታተልና በመቆጣጠር የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ እየተጋ ይገኛል ብለዋል።
ጉባኤው በዛሬው ውሎ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርትና የቀጣይ ዓመት ጠቋሚ ዕቅድ እንዲሁም ልዩ ልዩ አጀንዳዎች ቀርበው ይፀድቃሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በጉባኤው የጎፋ ዞን ህዝብ ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ አበበች መርጊያ፣ የደምባ ጎፋ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አንዳርጌ አራታ፣ የደምባ ጎፋ ወረዳ የመንግሥት ዋና ተጠሪ አቶ ሰማዬ ሻምበል፣ የደምባ ጎፋ ወረዳ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አበበ አማኔ ጨምሮ የወረዳው አጠቃላይ አመራሮች የወረዳው የምክር ቤት አባላት እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ