የክልል ተቋማት የሚዛን አማን ማዕከል የሴቶች ክንፍ ህብረት አባላት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ በደቡብ ቤንች ወረዳ በቂጤ ቀበሌ አካሄዱ

የክልል ተቋማት የሚዛን አማን ማዕከል የሴቶች ክንፍ ህብረት አባላት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ በደቡብ ቤንች ወረዳ በቂጤ ቀበሌ አካሄዱ

ሀዋሳ፡ ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የክልል ተቋማት የሚዛን አማን ማዕከል የሴቶች ክንፍ ህብረት አባላት የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ በደቡብ ቤንች ወረዳ በቂጤ ቀበሌ አካሂደዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ሀሳብ አመንጪነት የአየር ንብረትን የሚቋቋም የአካባቢ ስነ-ምህዳርን ማስጠበቅ የሚያስችል የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በየዓመቱ እየተከናወነ ይገኛል።

በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን ችግኞችን እንደሀገር ለማሳካት በተደረገው ጥረት ከ700 ሚሊየን በላይ በተሳካበት ማግስት አሁንም ተግባሩ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

በዚህም በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የክልል ተቋማት በመትከል ማንሰራራት በሚል መሪ ቃል የሚዛን አማን ማዕከል የሴቶች ክንፍ ህብረት አበላት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በደቡብ ቤንች ወረዳ በቂጤ ቀበሌ አካሂደዋል።

ለመጪው ትውልድ የአካባቢውን ሚዛን ሊጠብቅ የሚችልና የተፈጥሮ ሀብትን ለማውርስ በሚደረገው ጥረት ህፃናትም የራሳቸውን አሻራ አስቀምጠዋል።

በመርሃ ግብሩ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የተለያዩ ችግኞች በሴቶች ክንፍ ህብረት አበላት የተተከለ ሲሆን በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ የመሠረት ድንጋይ ተቀምጦ እየተከናወነ ያለውን የደንቢ ሎጅ ግንባታ ያለበት ደረጃም ተጎብኝቷል።

በፕሮግራሙ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ እና የክልሉ የሴቶች ክንፍ ፕሬዝዳንት ወይዘሮ ህይወት አሰግድ እንዲሁም የክልሉ ህብረት ስራ ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር ወይዘሮ ሰብለ ወዳጆና ሌሎች ሴት የህብረቱ አበላት ተሳትፈዋል።

ዘጋቢ፡ አብዲሳ ዮናስ – ከሚዛን ጣቢያችን