በክልሉ ውስን ቦታዎች የታዩ የፀጥታ ችግሮች ዕልባት እያገኙ መጥተዋል – ዋና አፈ ጉባዔ ፋጤ ስርሞሎ
ሀዋሳ፡ ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ ውስን ቦታዎች የታዩ የፀጥታ ችግሮች ዕልባት እያገኙ መጥተዋል ሲሉ የማዕከላዊ ኢትዮጵ ክልል የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ፋጤ ስርሞሎ ገለጹ፡፡
ክልሉን የወከሉ የፓርላማ አባላት እና የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ምክር ቤት አባላት በጋራ የህዝብ ውክልና ስራ ለማከናወን የሚያስችል የውይይት መድረክ በወልቂጤ ከተማ በማካሔድ ላይ ናቸው፡፡
ተመራጮች ወደ መረጣቸው ህዝብ ቀርበው ማወያየታቸው በመንግስትና በህዝብ መካከል ያለው ግንኙነት በማጠናከር ግልጽነትን ይፈጥራል ያሉት የክልሉ ህዝብ ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባዔ ፋጤ ስርሞሎ፥ በ2017 የበጀት አመት በተከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎች በክልልና በፌደራል ሊሰሩ የሚገባቸውን ጥያቄዎችን በማሰባሰብ ምላሽ ማሰጠት ተችሏል ብለዋል፡፡
በክልሉ ውስን አከባቢዎች አጋጥመው የነበሩ የፀጥታ ሁኔታ መሻሻሉን የገለጹት ወይዘሮ ፋጤ፥ ይህ ለውጥ እንዲመጣና የአስፈፃሚው አካል የሚጠበቅበትን እንዲወጣ የምክር ቤት አባላት ያደረጉት ክትትልና ድጋፍ ድርሻው ላቅ ያለ መሆኑን ዋና አፈ ጉባዔዋ አንስተዋል፡፡
በያዝነው የክረምት ወቅት የምክር ቤት አባላት ወደተመረጡበት አከባቢ በመሄድ በመንግስት የተከናወኑ ተግባራትን በመመልከት በህዝብ የሚነሱ ሃሳቦችን ይዞ በመመለስ ከአስፈፃሚው አካል ጋር በቀጣይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ: ሲሳይ ደበበ
በክልሉ ውስን ቦታዎች የታዩ የፀጥታ ችግሮች ዕልባት እያገኙ መጥተዋል – ዋና አፈ ጉባዔ ፋጤ ስርሞሎ

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ