ሴቶች በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ስለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች እና የሴቶች ውክልና በቁጥር ብቻ መተርጎም የለበትም-ፕሬዚደንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ

ሴቶች በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ስለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች እና የሴቶች ውክልና በቁጥር ብቻ መተርጎም የለበትም-ፕሬዚደንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ

ሴቶች በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ስለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች እና የሴቶች ውክልና በቁጥር ብቻ መተርጎም የለበትም ሲሉ ፕሬዚደንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ተናገሩ።

10ኛው የሴት የፖለቲካ መሪዎች ድርጅት ዓመታዊ ጉባዔ በአውሮፓ ህብረት ፓርላማ እና በቤልጂየም ፌዴራል ፓርላማ “ውክልና ወሳኝ ነው” በሚል መሪ ሀሳብ በጋራ ተካሂዷል።

የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ “ውክልና ወሳኝ ነው“ በሚል መሪ ሃሳብ በተጀመረው ጉባኤ ዋዜማ ላይ የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በንግግራቸውም ሴቶች በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ስለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች እና የሴቶች ውክልና በቁጥር ብቻ መተርጎም እንደሌለበት ተናግረዋል።

በጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ የ“ፈር ቀዳጅ ሴት” እውቅና ተበርክቶላቸዋል።

ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ በቤልጂየም ፓርላማ በተካሄደውና ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች አመራር ሴቶች በተገኙበት የሴት ፖለቲካ መሪዎች ድርጅት ዓመታዊ ጉባዔ ላይ ነው እውቅናው የተበረከተላቸው።

እውቅናው በኢትዮጵያ የመጀመሪያ ሴት ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸውን ጨምሮ ቀደም ሲል በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በተለያዩ የስራ ዘርፎች በነበራቸው ከፍተኛ የኃላፊነትና የመሪነት ሚና ፈር ቀዳጅ በመሆናቸውም ጭምር ያገኙት መሆኑ ተገልጿል።

ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር “ሽልማቱ ለብርቱዎቹ ሴቶች፣ በመጠለያ ጣቢያዎች ላሉት፣ ሕክምና ላይ ሆነው ሲጎበኟቸው የመማር ጉጉት እንዳላቸው ለነገሯቸው፣ ብቻቸውን ቤተሰብ የማስተዳደር ኃላፊነት ለተጣለባቸው እና ተስፋ ለሚሰጡን ባለ ተሰጥኦ የሀገሬ ሴቶች ይሁንልኝ” ብለዋል።

በንግግራቸውም ሴቶች በሰላም እና ደህንነት ዙሪያ ስለሚገጥሟቸው ተግዳሮቶች እና የሴቶች ውክልና በቁጥር ብቻ መተርጎም እንደሌለበት መናገራቸውን ከፕሬዚደንት ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያመላክትል።

የዘንድሮው ጉባኤ አስተናጋጅ ሀገር ቤልጂየም በአሁኑ ጊዜ በሴቶች አፈ ጉባኤዎች የሚመሩ ሁለት ምክር ቤቶች አሏት።