በጌዴኦ ዞን የ2017 በጀት ዓመት በሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕይዝ ዘርፍ የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑን የዞኑ ሥራና ክህሎት መምሪያ ገለጸ‎

‎በጌዴኦ ዞን የ2017 በጀት ዓመት በሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕይዝ ዘርፍ የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑን የዞኑ ሥራና ክህሎት መምሪያ ገለጸ‎

‎በበጀት ዓመቱ ለ32 ሺህ በላይ ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ጊዜያዊ እና ቋሚ የሥራ ዕድል መፈጠሩንም መምሪያው አስታውቋል።‎

‎የጌዴኦ ዞን ሥራና ክህሎት መምሪያ ተወካይና የገጠር ዘርፍ ኃላፊ አቶ መስፈን አለማየሁ፤ በበጀት ዓመቱ በዞኑ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው በመሥራት ላስመዘገቡት የተሻለ ውጤት ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዋንጫና ሰርተፊኬት ተሸላሚ መሆናቸውን አብራርተዋል።‎

‎በበጀት ዓመቱ 32 ሺህ 1 መቶ 91 ወጣቶች በጊዜያዊ እና ቋሚ ሥራዎች የሥራ ዕድል ተፈጥሯል ያሉት የመምሪያው ተወካይ፤ በግብርና፣ የኮሪደር ልማት፣ የአገልግሎት እና የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው ብለዋል።‎

‎4 መቶ 31 ሄክታር መሬት በከተማና በገጠር ለወጣቶች ተዘጋጅተው መተላለፋቸውን የገለጹት ተወካዩ፤ የገጠር መሬት ለሶስት ዓመት ሲሆን የከተማ መሬትና ሼድ ደግሞ ከሶስት እሰከ አምስት ለወጣቶች ይተላለፋል ብለዋል።‎

‎በዞኑ ቡሌ፣ ራጴና ጮርሶ ወረዳዎች ላይ ለተደራጁ ወጣቶች የወል መሬት ተሰጥቷቸው እያለሙ ውጤታማ በመሆን ሌሎች የሥራ ዕድል እየፈጠሩ ያሉ ወጣቶች እንዳሉ ገልጸዋል።‎

‎በቁጠባ፣ ሀብት መመደብና ብድሮችን በማስመለስ ለሥራ ፈላጊ ወጣቶች ገንዘብ ይሰራጫል ያሉት አቶ መስፍን፤ በበጀት ዓመቱ ከ24 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር ተሠራጭቶ ወጣቶች በተደራጁበት ዘርፍ እየሠሩ እንደሚገኙ ተናግረዋል።‎

‎ለወጣቶች ተሠራጭቶ ያልተመለሰ ከ1 መቶ 39 ሚሊዮን ብር በላይ ብድር መኖሩን የጠቁመት ተወካዩ፤ እነዚህን ብድሮች ለማስመለስ የሥራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ምክር ቤት ሰብሳቢ ዝናቡ ወልዴን (ዶ/ር) ጨምሮ ገዳዩ የሚመለከታቸው አካላት በትኩረት እየሠሩ መሆናቸውን አስረድተዋል።‎

‎ዘጋቢ፡ ተስፋዬ ጎበና – ከይርጋ ጨፌ ጣቢያችን