ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ በወልቂጤ ከተማ የሚገነባው የአትሌት ሰለሞን ባረጋ ሎጅ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ
ሎጁ የአካባቢውን ገጽታ በመቀየርና ለበርካቶች የሥራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረውም ተገልጿል።
በመርሃግብሩ ላይ የተገኙት የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ ሎጁ የአካባቢውን ገጽታ በመቀየርና ለበርካቶች የሥራ እድል በመፍጠር ከፍተኛ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
ለአትሌት ሰለሞን ባረጋ በሽልማት በተበረከተለት በ15 ሺህ ካሬ ቦታ ላይ የሚገነባው ሎጁ ከሁለት እስከ ሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል።
የወልቂጤ ከተማ ከንቲባ አቶ ሙራድ ከድር የወልቂጤ ከተማን ለማልማት ለተጀመረው እንቅስቃሴ የሎጁ መገንባት ትልቅ ሚና አለው ብለዋል።
በተቀመጠው ጊዜ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግም ጠቁመዋል።
አትሎት ሰለሞን ባረጋ በበኩሉ አካባቢውን ለማልማት ካለው ቁጭት በመነሳት ወደ ልማቱ መግባቱንና በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ለአገልግሎት እንዲበቃ የአካባቢው ማህበረሰብ በባለቤትነት እንዲያግዘው ጠይቋል።
ደረጃውን የጠበቀና ባለ አምስት ኮከብ ሎጅ ግንባታ ከ300 ሚሊዮን ብር በላይ እንደሚፈጅ ተጠቁሟል።
ዘጋቢ፣ ተረፈ ሀብቴ

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ