በተቋማትና በባለሙያዎች መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ

በተቋማትና በባለሙያዎች መካከል የውድድር መንፈስ በመፍጠር ቀልጣፋና ፈጣን አገልግሎት መስጠት እንደሚገባ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የቀቤና ልዩ ወረዳ አስተዳደር አስታወቀ

የወረዳው ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ማጠቃለያ ግምገማ የዕውቅናና የምስጋና መድረክ ተካሂዷል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪና ፍትህ ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ አብዱልማሊክ አብደላህ በዚሁ ወቅት እንደገለፁት፤ በ2017 በጀት አመት በልዩ ወረዳው ተቋማት የነበሩ ጠንካራ ጎኖችን በማስቀጠልና ጉድለቶችን በማረም በ2018 ዓ.ም የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መረባረብ ይገባል።

በተለይም የመልካም አስተዳዳር ችግሮችን በመቅረፍ የአገልግሎት አሰጣጡን ቀልጣፋና ፈጣን ለማድረግ በትኩረት መስራት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የቀቤና ልዩ ወረዳ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት ሃላፊ ወ/ሮ ሂክማ ጀማል በበኩላቸው፤ በ2017 በጀት ዓመት በልዩ ወረዳው የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችንና ብልሹ አሰራሮችን በመቅረፍ በተቋማት የተሻለ አሰራር በመዘርጋት በተከናወኑ የሪፎርም ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡን አስረድተዋል።

የመድረኩ ዋና ዓላማ በልዩ ወረዳው ተቋማትና ባለሙያዎች መካከል የውድድርና የፉክክር መንፈስ በመፍጠር በቀጣይ የተሻለ የስራ አፈፃፀም ማስመዝገብ ማስቻል መሆኑንም ወ/ሮ ሂክማ ተናግረዋል።

በመሆኑም በቀጣይ በየደረጃው የሚገኙ ተቋማት፣ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት በማድረግ መረባረብ እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።

በመድረኩ ላይ የልዩ ወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የ2017 በጀት አመት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል::

በ2017 በጀት ዓመት ባስመዘገቡት የስራ አፈፃፀም የእውቅና የምስጋና ሰርተፊኬት በማግኘታቸው መደሰታቸውንና በቀጣይ ለማህበረሰቡ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚተጉ ከየሴክተሩ የተውጣጡ የመድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።

በመድረኩ የልዩ ወረዳ እንዲሁም የቀበሌ አመራሮችና ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን በ2017 በጀት ዓመት የተሻለ አፈፃፀም ላስመዘገቡ የልዩ ወረዳው ተቋማት፣ አመራሮችና ባለሙያዎች የእውቅናና የምስጋና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

ዘጋቢ፡ መሀመድ ፈይሳ – ከወልቂጤ ጣቢያችን