”የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” – ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ
”የምንተክላቸው ችግኞች ለትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋትን የሚያስገኙ ናቸው” ሲሉ የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ ገለጹ፡፡
የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ ዘንድሮ ”በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በክልሉ በአንድ ጀንበር 8 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሃ ግብር በሰሜናዊ ሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ አልዳዳ ዴላ ቀበሌ አስጀመሩ::
በቦርቻ ወረዳ 506 ሺህ 115 ችግኞችን ለመትከል 133.7 ሄክታር መሬት በ8 የመትከያ ቦታዎች 34 ሺህ በላይ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከማለዳው ጀምሮ በነቂስ በመውጣት የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር እያካሄዱ ይገኛሉ።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ በወረዳው በአልዳዳ ዴላ ቀበሌ ተገኝተው ችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ሲያስጀምሩ ባደረጉት ንግግር መሬት ስትራቆት ለህይወት አስጊ መሆኑን ጠቅሰው የተሻለ የአየር ንብረት ለውጥ እንዲመጣ አካባቢያችንን ለማስዋብና ለኑሮ ምቹ ለማድረግ እንዲሁም በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚመጣውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቋቋም ችግኝ ተከላን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ አክለውም የችግኝ ተከላ ተግባር የትም ቢሆን በአንድ ጀንበር ብቻ በማካሄድ የሚያበቃ ሳይሆን ከዚህ በፊት በየአካባቢያችን የተተከሉትን እየተንከባከብን ዘንድሮም በአረንጓዴ አሻራ የበኩላችንን በመወጣት ለነገ ትውልድ ተሻጋሪ ትሩፋት እናስቀምጥ በሚል መልዕክታቸውን ማስተላለፋቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን የተገኘ መረጃ ያመለክታል።
More Stories
ከማረምና ማነጽ ጎን ለጎን የሀገሪቱን አረንጓዴ ልማት እስትራቴጂን ለማሳካት ሚናውን እንደሚወጣ የጂንካ ማረሚያ ተቋም አስታወቀ
“በክልሉ ባለፉት አመታት የተተከሉ ችግኞች ለኢኮኖሚ እና የስራ ዕድል ፈጠራ ምንጭ ሆነዋል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ/ር) ክልላዊ የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ አስጀመሩ