ከማረምና ማነጽ ጎን ለጎን የሀገሪቱን አረንጓዴ ልማት እስትራቴጂን ለማሳካት ሚናውን እንደሚወጣ የጂንካ ማረሚያ ተቋም አስታወቀ
“በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የጂንካ ማረሚያ ተቋም ፖሊስ አባላትና ታራሚዎች የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላ አካሂደዋል።
የሚተከለውን ችግኝ በመንከባከብና ለአካባቢውና ለአለም አቀፍ አየር ንብረት ለውጥ እንዲሻሻል የተጀመረውን የአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ በተጠናከረ መልኩ ይሰራል ያሉት የጂንካ ማራሚያ ተቋም አዛዥ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ነሬሬ፡፡
በተቋሙ የግብርና ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ብዙነሽ አገኘሁ፤ በማረሚያ ተቋሙ ለምግብነትና ለሌሎች አገልግሎቶች የሚውሉ ችግኞች እየተተከሉ መሆኑን ጠቁመው የጽድቀት መጠናቸውም በተሻለ ሁኔታ እንዲቀጥል ውሃ የማጠጣትና የመንከባከብ ተግባራት እየተከናወነ መሆኑን ተናግረዋል።
የጂንካ ማረሚያ ተቋምን ጨምሮ በኣሪ ዞን በአንድ ጀንበር 4 ሚሊዮን 201 ሺህ 452 በላይ ችግኝ እየተተከለ ይገኛል።
ዘጋቢ: ጄታ ታገሠ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
የአፈር ጤናን በመጠበቅና ለምነትን በማሻሻል የአርሶ አደሮችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ምርምር ኢኒስቲትዩት የወራቤ ግብርና ምርምር ማዕከል አስታወቀ።
የሕዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል – የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ተስፋዬ በልጅጌ (ዶ/ር)
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ