ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ነገ ሐምሌ 24/2017 “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሔደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ህዝብ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ነገ ሐምሌ 24/2017 “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሔደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ህዝብ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ፡፡
በአገር አቀፍ ደረጃ 700 ሚሊዮን በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ደግሞ 6 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር መትከል የሚያስችል ዝግጅት መጠናቀቁን ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።
ይህን ሀገራዊ ጥሪ ከግብ ለማድረስ የክልሉ ህዝብ በነቂስ በመውጣት አሻራውን ማሳረፍ እንዳለበት ርዕሰ መስተዳድሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመለክታል።

More Stories
በሩብ ዓመቱ 3.7 ቢሊየን ብር መሰብሰቡን የክልሉ ፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ወይዘሮ ወሰነች ቶማስ ገለጹ
የማር ምርት እጅግ ተጠቃሚ እንደሚያደርግ በጎምቦራ ወረዳ በንብ ማነብ ስራ የተሠማሩ አርሶአደሮች ተናገሩ
ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሰ የግብርና ልማት ላይ አደጋ እንዳያስከትል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለጸ