በጥረቱ ውጤታማ የሆነው ወጣት ተሞክሮ!
በበየነ ሰላሙ
ጥቂት የማይባሉትና የወጣትነት ትርጉሙ ኃይል፣ ብርታትና ለውጥ ነው ያሉት ለተሻለ ነገ ዛሬን ሲታትሩ፣ ሲለፉና ሲደክሙ ይታያል፡፡
አሁን ያለንበት ዘመን አዲስ ሃሳብ የሚፈልቅበት ታግሎ ለአሸናፊነት የሚበቃበት ነውና፤
በዚህም በወጣትነት ዘመናቸው ስኬታማ ህይወትን የተቀዳጁ በርካቶች ናቸው፡፡
ይህንን መነሻ በማድረግ ጠንክሮ በመሰራት ሀብት ንብረት ማፍራት የቻለ ወጣት ተሞክሮ ልናስቃኛችሁ ወደናል ፡፡
ተወልዶ ያደገው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሀዲያ ዞን ግቤ ወረዳ ሜጋቾ ቀበሌ ነው፡፡ ወጣት ኤርሚያስ መለሰ እድሜው ለትምህርት ሲደርስም ከእድሜ እኩዮቹ ጋር ቀለም ቆጥሯል፡፡
የከፍተኛ ደረጃ ትምህርቱን በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በኢኮኖሚክስ ትምህርት አጠናቅቆ በመንግሥት ስራ ተቀጥሮ ለ2 ዓመታት ያህል ከሰራ በኋላ ወደ ግል ስራ ተሸጋግሯል፡፡
ወጣት ኤርሚያስ በእችላለሁ መንፈስ ነገሮችን ወደፊት መመልከት የተሻለ እድልን እንደሚያጎናጽፍ ያምናል፡፡
ጠንክሮ መማሩና በተለያዩ የግል ኢንደስትሪዎች አካበቢ በመስራት ያካበተው ልምድ እንደጠቀመው ያነሳል፡፡
በኢንዱሰትሪ ኮርፖሬሽን በተመቻቸ እድል ተጠቅሞ ዛሬ ኤርሚያስ መለሰና ቤተሰቡ የደረቅና ፈሳሽ ሳሙና ፋብሪካ ባለቤት ለመሆን በቅቷል::
የተማርከው፣ የዋልክበት፣ የኖርክበት ሁኔታ ለውሳኔዎች መነሻ ነው የሚለው ወጣት ኤርሚያስ መለሰ ትንሽ ያጠራቀመውን ገንዘብ እና ሀሳብ መነሻ በማድረግና ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ በብድር በተገኘው መነሻ በ2015 ዓ.ም ስራ መሰማራቱን ገልጿል፡፡
የፋብሪካ ስራው እንዳሰበው አልጋ በአልጋ አልሆነለትም፡፡ ፈተና የሌለው ዓለም ስለሌለ ፈተና ለቀጣይ ጉዞአችንና ለምንደርስበት እድገት መነሻ ነው ይላል ወጣት ኤርሚያስ::
ሀሳብን መነሻ በማድረግ የተጀመረው ደረቅ እና ፈሳሽ የሳሙና ፋብሪካ ዛሬ ላይ ከ60 እስከ 70 ለሚሆኑ ወጣቶች ቋሚና ጊዜያዊ የስራ እድል መፍጠሩንም ወጣት ኤርሚያስ ጠቁሟል::
ወጣት ኤርሚያስ ስራ እድል ከመፍጠር በተጨማሪ የቴክኖሎጂ ሽግግርም ለወጣቶቹ እያደረገ ነው::
ሌሎች ወጣቶችም ተስፋ ከመቁረጥና ስደትን አማራጭ ከማድረግ ይልቅ ስራ ፈጥሮ በመስራት ተስፋ ባለመቁረጥና ትዕግስት በተሞላ መልኩ ከሰሩ ቀስ በቀስ መለወጥና ትልቅ ደረጃ መድረስ ይችላሉ የሚል ምክረ ሀሳቡንም አጋርቷል።
More Stories
ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) ነገ ሐምሌ 24/2017 “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ሀሳብ በሚካሔደው የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የክልሉ ህዝብ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረቡ
ምክር ቤቱ ለ2018 በጀት ከ578 ሚሊዮን ብር በላይ ማጽደቁ ተገለጸ
የግብርና ዘርፍ የእሴት ሰንሰለትን በመከተል የስራ ዕድልን መፍጠር በኢኮኖሚው ላይ ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ቢሮ ገለፀ