ሀምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም 60 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ

ሀምሌ 24 ቀን 2017 ዓ.ም 60 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ አስታወቀ

በዕለቱ ለሚከናወነው የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር የችግኝና የጉድጓድ ዝግጅት መጠናቀቁን በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የዲላ ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ሀላፊ መሪሁን ፍቅሩ(ዶ/ር) ገልፀዋል።

በ2017 ዓ.ም በበልግና በክረምት 394 ሚሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የጠቀሱት ሀላፊው፤ በአንድ ጀምበር የተከላ መርሀ ግብር 60 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉ አስታውቀዋል።

የህብረተሰብ አቀፍ ንቅናቄውን በማጠናከር የታለመው ዕቅድ ዳር እንዲደርስ ስራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውንም ሀላፊው ጠቁመዋል።

በዕለቱ ከማለዳው ጀምሮ በሁሉም የተመረጡ የክልሉ አካባቢዎች የተከላ መርሀ ግብሩ የሚከወን ሲሆን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የችግኝ ዝርያዎች ይተከላሉ ተብሏል።

ሀምሌ 24 ቀን በሚደረገው የአንድ ጀምበር የተከላ መርሀ ግብር በተመረጡ 973 ቦታዎች 9421 ሄክታር መሬት ላይ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር እንደሚከናወንም ሀላፊው ጠቁመዋል።

የክልሉ ህዝብ ከማለዳው ጀምሮ አሻራውን እንዲያኖርም ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ: ባዬ በልስቲ