ሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር ያለምንም ችግር እንዲካሄድ በቂ ዝግጅት መደረጉን የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ገለፁ
ዝግጅቱን አስመልክቶ መግለጫ የሰጡት የኣሪ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አብርሃም አታ ኣሪ ዞን የሠላም ተምሳሌት ፤ህዝቦቿ እንግዳ ተቀባይ በመሆናቸው ወደ ዞኑ የሚመጡ የስፖርት ልዑካን ቡድን ወደ ሁለተኛ እቤታቸው እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።
በአሁን ወቅት ከሀገሪቱ አራቱም ማዕዘናት የስፖርት ልዑካን ቡድን ወደ ጂንካ ከተማ እየገቡ ሲሆን መላው የአካባቢው ህዝብ እንግዶችን ተቀብለው እንዲያስተናግዱ ጥሪ አቅርበዋል።
በተለይ እንዲህ ዓይነት ውድድሮች ኢትዮጵያዊያን በመላው ሀገሪቱ ተዘዋውረው ኢትዮጵያን ለመገንዘብ ትልቅ ዕድልን ይፈጥራል ሲሉም ዋና አስተዳዳሪው ገልፀዋል።
የኣሪ ዞን ፓሊስ አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር መሠለ ገብሬ እና የኣሪ ዞን ሠላምና ፀጥታ መምሪያ ሀላፊ አቶ ማታዶ በርቢ በጋራ እንደገለፁት ስፖርታዊ ውድድሩ ያለምንም ችግር እንዲጠናቀቅ በቂ ዝግጅት ተደርጎ የስፖርት ልዑካኑን ቅበላ እየተደረገ እንዳለ አስረድተዋል።
አጠቃላይ የፀጥታው መዋቅር ለውድድሩ ስኬት ሀላፊነቱን እንደሚወጣ የገለፁት የመንግስት የሥራ ሀላፊዎች ይህንን ከመላው የአካባቢው ህዝብ ጋር በጋራ ቅንጅት እየተሠራ ስለመሆኑም ተናግረዋል ።
የአካባቢው ነዋሪዎችም እንግዶችን ተቀብለው በማስተናገድ ውድድሩ እስኪጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች ሁሉ ከጎናቸው እንደሚቆሙ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።
ሀገር አቀፍ የክለቦች ሻምፒዮና ውድድር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በኣሪ ዞን አስተናጋጅነት ከሰኔ 28/2017 ዓ/ም ጀምሮ ለአንድ ወር ያህል እንደሚቆይ ተገልጿል ።
ኣሪ ዞን ጂንካ ከተማ በቅርቡ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የክለቦች ሻምፒዮና ውድድርን ማስተናገዱ የሚታወስ ነው።
ዘጋቢ:-ተመስገን አበራ-ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
ዳራማሎ ደንዳሾ ስፖርት ክለብ ባስኬት ቡናን በማሸነፍ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና የዋንጫ አሸናፊ ሆነ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ዛሬ በተደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ለፍፃሜ ያለፉ ክለቦች ተለይተው ታውቀዋል
ስፖርት የወንድማማችነት እና የልማት መጠናከር አንዱ ማሳያ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ አስታወቀ