ቢሮው የone wash እና co-wash ፕሮግራሞች ተጠቃሚ ለሆኑ ዞኖችና ልዩ ወረዳዎች ፋይናንስ ሴክተር ለሚሰሩ ባለሙያዎችና አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና በወልቂጤ ከተማ ሰጥቷል።
የጉራጌ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብዶ ሀሰን በእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግራቸው በone wash እና co-wash የሚተገበሩ ፕሮግራሞች እንደ ፋይናንስ ሴክተር ትልቅ አጋዦች መሆናቸውን ጠቁመዋል።
በመሆኑም ከረጂ አካላት የምናገኛቸው እገዛዎችን በአግባቡ ተግባር ላይ እንዲውሉ የተጣለብንን ኃላፊነት በተገቢው ልንወጣ ይገባልም ብለዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ በመንግስት ፋይናንስ ዘርፍ የቻናል አንድ ፕሮግራሞች ማስተባበሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ታረቀኝ ኑራሙ በሥልጠናው ወቅት እንዳሉት፤ ሁለቱም ፕሮግራሞች በውኃ አቅርቦት እንዲሁም በግልና አካባቢ ንጽህና አጠባበቅ ላይ ትኩረት አድርገው ይሰራሉ።
የህዝቡን የልማት ፍላጎት በመንግስት በጀት ብቻ ማሟላት የሚቻል ባለመሆኑ በእነዚህ ፕሮግራሞች የሚገኘው ድጋፍ የበጀት እጥረትን በማቃለል ህብረተሰቡን ተጠቃሚ በማድረግ ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ገልጸዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የone wash ፕሮጀክት የሒሳብ ዩኒት ቡድን መሪ አቶ ዳዊት ዘርጋ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ በክልሉ በሚገኙ 21 ወረዳዎችና አንድ ከተማ አስተዳደር ላይ የሚተገበር ነው ብለዋል።
ፕሮጀክቱ የሚተገበርባቸው ዞኖች 15 በመቶ የግዴታ መዋጮ ሲያደርጉ 85 በመቶ ተጨምሮ በሚላክላቸው በጀት የሚተገበር ፕሮጀክት ሲሆን በዘንድሮ ዓመትም እስካሁን ባለው አፈጻጸም የዞኖች ተሳትፎ ዝቅተኛ መሆኑን ገልጸዋል።
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ የco-wash ፕሮጀክት ፋይናንሽያል ማኔጅመንት ስፔሻሊስት የሆኑት አቶ ተስፋሁን በሃሩ በበኩላቸው፤ ፕሮጀክቱ ከፍተኛ የውኃ ችግር ባለባቸው 7 ወረዳዎች በመተግበር የህብረተሰቡን ችግር ማቃለል መቻሉን ተናግረዋል።
የone wash ፕሮጀክት በመንግስት የበጀት አቅም ተደራሽ ማድረግ ያልተቻሉ ልማቶችን በመተግበር የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ ትልቅ እገዛ እያደረገልን ነው ሲሉ በሥልጠና ወቅት ያነጋገርናቸው የስልጤ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ አቶ አብድረዛቅ አማን፣ የሃላባ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ዙበይዳ ገለቱ እና የማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሻምበል አበበ ተናግረዋል።
በሥልጠናው በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ የone wash እና co-wash ፕሮግራሞች ተጠቃሚ የሆኑ ዞኖችና፣ ልዩ ወረዳዎች ፋይናንስ ሴክተር ባለሙያዎችና አመራሮች ተሳትፈዋል።
ዘጋቢ፡ ተረፈ ሀብቴ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ