በደቡብ ኦሞ ዞን በማሌ ወረዳ በሌሞ ካለንዶ ቀበሌ 566 ሄክታር መሬት ለማልማት የማህብረሰብ አቀፍ የተፋሰስ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሄደ
የማሌ ወረዳ መስኖና ቆላማ አካባቢ ልማት ጽ/ቤት ከቆላማ አካባቢ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት ምዕራፍ ሁለት ከማሌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ጋር በጋራ በመተባበር በሌሞ ካለንዶ ቀበሌ ልዩ ስሙ “ጱሎ ባኮ” ንዑስ የተፋሰስ ልማት ስፍራ የተፋሰስ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
የማሌ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ተከስተ በንግግራቸው የወረዳው ቆላማ ኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት በዘንድሮ በሌሞ ካለንዶ ቀበሌ 566 ሄክታር መሬት በተፋሰስ ለማልማት ግብ ጥሎ እየሠራ ሲሆን 250 በላይ የህብረተሰብ ክፍሎችንም ያሳተፈ ነው ብለዋል።
ኃላፊው አክለውም ፕሮጀክቱ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ ለአደጋ ተጋላጭ የሆኑ የተራቆቱ አካባቢዎችን በተፋሰስ በማልማት፣ የግጦሽ መሬት አጠቃቀምና ማህብረሰቡ ከተፈጥሮ አደጋ ስጋት ነፃ ሆኖ በዘላቂነት የኑሮ ዘይቤን ይዞ እንዲቀጠሉ የማድረግ ስራ በስፋት መስራቱንም አንስተዋል።
የተፋሰስ ልማት ሥራ እንደወረዳ ከተጀመረ 15 ዓመታት መሆኑን ያነሱት የማሌ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አልጋጋ ባልንሴ፤ በዚህ ጊዜ ዉስጥ በተፋሰስ የታዩ በርካታ ተጨባጭ ለዉጦች መኖራቸውን በማንሳት በዛሬዉ ዕለት በዚህ ስፍራ የተገኘዉን ይህንን ሥራ ለማጠናከር እና እዉቅና ለመስጠት ነው ብለዋል።
በተፋሰስ ልማት ተሳታፊ ከሆኑት ከቀበሌ ነዋሪዎች መካከል አቶ ኢያሱ ጃርባነና አቶ ሱልጣን ሲሳይ በሰጡት አስተያየት፤ ከዚህ በፊት የተፋሰስ ልማት በማንስራበት ጊዜ የጎርፍና የአካባቢ መራቆት ተጽኖ ስር እንደነበሩ ተናግረዉ አሁን ቀበሌያቸው በመንግስትና በኘሮጀክቱ እገዛ በተፋሰስ የታየዉን አየር ንብረት ለዉጥ በእጅጉ እንዳረካቸዉና ተሳትፏቸውን እንደሚያጠናክሩ ተናግረዋል።
ዘጋቢ: ገጶስ አየለ – ከጂንካ ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ