ሀዋሳ፣ ሰኔ 10/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ከተሞች የብልጽግና መገለጫ እንዲሆኑ እየተሰራ መሆኑን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ ተናገሩ።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በጌዴኦ ዞን የቡሌ ከተማ አስተዳደር ምስረታ ተካሂዷል።
የከተማ አስተዳደር መዋቅር መመስረቱ ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለውም ተገልጿል።
ዛሬ የተከናወነው የምረቃ ስነስርዓት ከዚህ ቀደም የተጠራቀመ የህዝብ ጥያቄ በብልጽግና መንግስት ምላሽ ያገኘበት ነው ያሉት የቡሌ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ በራቆ በራሶ ከተማው የፈርጅ ለውጥ ጥያቄ ምላሽ በማግኘቱ መደሰታቸውንም ተናግረዋል።
የቡሌ ከተማ አስተዳደርን ስንመሰርት ህዝቡ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ በአቅራቢያው እንዲያገኝ ለማስቻል ነው ያሉት የጌዴኦ ዞን አስተዳዳሪ ዶ/ር ዝናቡ ወልዴ ከተማው ያለውን ሀብት በአግባቡ ተጠቅሞ እንዲያለማ ጠቁመዋል።
የአካባቢው ባለሀብትና ሌሎችም ወደ ከተማዋ በመምጣት ኢንቨስት እንዲያደርጉ የጠየቁት የዞኑ አስተዳዳሪ ዞኑ በሚፈለገው ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግም ተናግረዋል።
የደቡብ ኢትዮጽያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አበባየሁ ታደሰ በበኩላቸው፤ ከተሞች የብልጽግና መገለጫ እንዲሆኑ ዕድሜ ጠገብና ለኑሮ ምቹ ያልሆኑ ከተሞችን እንደገና የመስራት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ከተሞች ዜጎች ተደላድለው የሚቀመጡባቸውና የሚንቀሳቀሱባቸው እንዲሆኑ ለማስቻል እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
የቡሌ ከተማ ለዚህ በመብቃቱ እንኳን ደስ አላችሁ ያሉት ምክትል ርዕሰመስተዳደሩ ገቢን አሟጦ መሰብሰብና ህብረተሰቡ አካባቢውን እንዲያለማ ጥሪ አስተላልፈዋል።
የቡሌ ከተማን ወደ ከተማ አስተዳደርነት ስናስገባ ለዓመታት ያቆየችው ሀብት ታይቶ መሆኑን የገለጹት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከተማና መሰረተልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ብርሃኑ ዘውዴ ህብረተሰቡ ከተማዋን ከዚህ ቀደም ከነበረው በበለጠ እንዲያለማ አሳስበዋል።
የ137 ዕድሜ ባለጸጋዋ ቡሌ ዛሬ ቀን ወጣላት የሚሉት የአካባቢዋ ነዋሪዎች የከተማ አስተዳደር ምስረታ በመካሄዱ መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ውብሸት ካሳሁን – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ