የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የስራ አንቅስቃሴን ምልከታ አድርገዋል፡፡
ኘሬዝዳንቱ በክሉ በነበራቸው ቆይታ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር የተወያዩ ሲሆን ከክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች ጋር በካሄዱት የውይይት መድረክ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ኘሬዝዳንት አቶ ጥላሁን ታደመ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ከተዋቀረ ወዲህ እየሰጠ ባለው አገልግሎትና ባጋጠሙት ተግዳሮቶች ዙሪያ ጽሁፍ አቅርበው ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
በውይይቱ ላይ የተሳተፉት ዳኞችም በቴክኖሎጂ አጠቃቀም፣ የዳኞ የአቅም ማጐልበት፣ የዳኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንዲሁም በሌሎች በጠቅላይ ፍርድቤቱ በጉድለት ይታያሉ ያሉዋቸው የቁሳቁስና የፋይናሻል እጥረት ዙሪያ ጥያቄ አቅርበው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ኘሬዝዳንት ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው የለውጥ ፍኖተ ካርታ ተዘጋጅቶ ክልሎች እየተገበሩ መሆናቸውን ጠቁመው ይህም ያለበት ደረጃ እየተገመገመ የተሻለ አፈፃፀም እንዲመዘገብ እየተሰራ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም እየተሰጠ ያለው የዳኝነት አስተዳደር ምን እንደሚመስል ድጋፍ ለመስጠት መምጣታቸውንም ገልጸዋል።
የለውጥ ፍኖተ ካርታ መተግበር ከተጀመረበት ጊዜ ወዲህ የሚነሳው አንዱ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም መሆኑን ኘሬዝዳንቱ አቶ ቴዎድሮስ ምህረት አውስተው ለዚህም የቴክኖሎጂ መተግበሪያ ግብዓት የሰው ኃይልና የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ ቆጭቶ ገብረማርያም በበኩላቸው ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ቴክኖሎጂ በመጠቀም የዳኝነት አስተዳደር ስራን በተቀላጠፈ መንገድ ለመስራት ያስችል ዘንድ አስፈላጊውን ቁሳቁስ ለማሟላት የክልሉ መንግስት ቃል የገባላቸው መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ ቴዎድሮስ ምህረት በክልሉ ቤንች ሸኮ ዞን በኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ኢንሼቲቭ እየተገነቡ ያሉትን የደንቢ ሎጅንና የሚዛን አማን አለም አቀፍ አውሮኘላን ማረፊያ ግንባታ ተዘዋውረው የጐበኙ ሲሆን በተለይ የአውሮኘላን ማረፊያ ግንባታው ከተጠናቀቀ በክልሉ የሚሰጠውን የፍትህ ተደራሽነትን የተሳለጠ በማድረግ ድርሻው የጐላ ይሆናል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ወሰኑ ወዳጆ ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ