የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ በጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት አፈጻጸም ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ውይይት እያካሄደ ይገኛል

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ በጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት አፈጻጸም ዙሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በወልቂጤ ከተማ ውይይት እያካሄደ ይገኛል

የጉራጌ ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ መብራቴ ወልደማርያም መድረኩ በከፈቱበት ወቅት እንደገለፁት፤ በዞኑ የጉራጊኛ ቋንቋ በትምህርት ስርዓት ውስጥ ተቀርፆ ስራ ላይ ለማዋል መምሪያው ካለፉት ሶስት አመታት ጀምሮ በርካታ ተግባራት ሲያከናወን ቆይቷል።

በ2017 በጀት አመት በጉራጊኛ ቋንቋ ትምህርት በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የነበሩ ጠንካራ ተግባራትን በማጠናከርና ጉድለቶችን በማረም በቀጣይ የተጠናከረ ስራ መስራት ይጠበቃል ሲሉም ተናግረዋል።

በመድረኩ የጉራጌ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ደሳለኝ ፈቀደ፣ የዞኑ ምክር ቤት የማህበራዊ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ጥሩነሽ ምኑታ፣ የዞኑ ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሃላፊ ወይዘሮ መሰረት አመርጋን ጨምሮ የከተማ አስተዳደር፣ የወረዳዎች የትምህርት ጽ/ቤትና የባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ሃላፊዎችና ሌሎችም በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።

ዘጋቢ፡ እርካብነሽ ወ/ማርቆስ – ከወልቂጤ ጣቢያችን