በዩኒቨርስቲው የተደረገው የሪፎርም ስራ ለውጥ ያስገኘ መሆኑን የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች ገለጹ
ዩኒቨርሲቲው ከመማር ማስተማር ስራው ባለፈ ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በማጠናቀቅ ወደ ስራ እንዲገቡ መደረጉም ተጠቁሟል።
ሁለተኛ ትውልድ እየተባሉ ከሚጠሩ ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ ተጠቃሽ ነው የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርሲቲ።
የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች እንደሚገልጹት በግቢው በርካታ ችግሮች እንደነበሩ አውስተው መንግስት የአመራር ሪፎርም ካደረገ በኋላ በአንድ አመት ውስጥ በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች ለውጥ ተመዝግቧል።
በተለይም ለረጅም ጊዜያት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን ለመጨረስ የተሰራው ስራ ውጤታማ ነው ብለዋል።
ተቋርጠው የነበሩ የውስጥ ለውስጥ የአስፓልት መንገዶች እና ህንጻዎች መገንባታቸው ለአብነት የሚጠቀስ እንደሆነ ጠቁመዋል።
ለመማር ማስተማሩ ስራ ስኬታማ እንዲሆንም ችግሮቹን ለመፍታት የሚደረገው ጥረት መልካም የሚባል ነውም ብለዋል።
የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ የምርምር እና ጉድኝት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ዶክተር ግርማ ጥላሁን በበኩላቸው፤ ሪፎርም የተደረገበት አዲሱ የለውጥ አመራር ስራ በጀመረ በአጭር ጊዜ ውስጥ በግቢ የነበሩ ችግሮችን በመለየት በአጭር እና በረጅም ጊዜያት ለመፍታት በማቀድ ወደተግባር መገባቱን ተናግረዋል።
በዚህም በግቢው ለበርካታ ጊዜያት ተጀምረው ያልተጠናቀቁ ፕሮጀክቶችን በመለየት እንዲጠናቀቁ የማድረግ ስራ ተሰርቷልም ብለዋል።
ህብረተሰቡ የሚያነሳው የምርምር እና የማህበረሰብ አቀፍ የጉድኝት ስራዎችን በመለየት ምላሽ ለመስጠት መሰራቱን ጠቁመዋል።
ለአብነትም ከአስራ ሁለት ሚሊዬን ብር በላይ ወጪ በማውጣት ሊተገበሩ የሚችሉ የምርምር ስራዎችን ለማከናወን ወደተግባር የተገባ ሲሆን ለአብነትም የቴፒ ከተማ የውሃ እጥረት በዘላቂነት ለመቅረፍ እና የሾንጋን ወንዝ አሳ የማርባት የምርምር ስራ ወደተግባር እንዲገባ ተደርጓል ብለዋል።
ትልቅ ወጪ የወጣበት የሚዛን ቴፒ ዩኒቨርስቲ ማስተማሪያ ሆስፒታል አገልግሎት ሳይሰጥ የቆየውን የሲቲ ስካን ማሽን አሁን ለአገልግሎት ዝግጁ መደረጉን ጠቁመዋል።
በአጭር ጊዜ የመጡ ለውጦችንም ከግቢ ማህበረሰብ እና ከአካባቢው ህዝብ ጋር ተቀናጅቶ ይበልጥ ለውጡን ተጠናክሮ እንደሚተገበርም ዶክተር ግርማ ተናግረዋል።
ዘጋቢ: አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ