ሰላምን  በማስጠበቅ እና ልማቱን በመደገፍ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲሚወጡ  በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚገኙ የወጣቶች ክንፍ አባላት ተናገሩ።

ሰላምን  በማስጠበቅ እና ልማቱን በመደገፍ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲሚወጡ  በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል የሚገኙ የወጣቶች ክንፍ አባላት ተናገሩ።

ከክልሉ ከሁሉም ዞኖች ለተውጣጡ ወጣቶች  በሚዛን አማን ከተማ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በስልጠናው እየተሳተፉ የሚገኙ ወጣቶች እንደተናገሩት ስልጠናው በቂ ክህሎት እንዲጨብጡ ከማድረግ በዘለለ ሀገራዊ ትርክቶችን ለማስቀጠል እንዲሁም ለጋራ ሀገር የጋራ መግባባት ይፈጥራል።

ሰላምን በማስጠበቅ በኩል የወጣቱ ድርሻ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረው የበኩላቸውን እንደሚወጡ ጠቁመዋል።

ወጣቱ ከስራ ጠባቂነት በመውጣት በአካባቢ ያሉትን እምቅ የተፈጥሮ ሀብቶችን ወደኢኮኖሚ በመቀየር ወደስራ ፈጣሪነት እንዲገባም ያሉትን እድሎች አሟጦ መጠቀም ይጠበቅበታልም ብለዋል።

ሚዛናዊ በሆነ መንገድ ሚዲያን መጠቀም ያሉት ወጣቶቹ ከስሜተኝነት በጸዳ መልኩ ለበጎ ተግባር ማዋል ይገባልም ብለዋል።

በተቋማት ግንባታ እና በወጣቱ ተጠቃሚነት ዙሪያ የተጀመሩ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተናገሩት ደግሞ የደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልል የወጣቶች ክንፍ ሀላፊው አቶ ሰይድ ኢብራሂም  ናቸው።

ወጣቱ እንደ ሀገር ለመጣው ለውጥ የበኩሉን ድርሻ አበርክቷል ያሉት ኃላፊው የመጣውን ለውጥ ለማስቀጠል ደግሞ ወጣቱን አሳታፊ በማድረግ የወጣቱን አቅም መጠቀም ይገባል ብለዋል፡፡

በተቋማት ግንባታ እና ሀገራዊ ትርክቶችን በማስቀጠሉ ዙሪያ የጋራ ግንዛቤ ለመፍጠር የውይይት መድረኩ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ዘጋቢ፤ አብዮት በቀለ ከሚዛን ጣቢያችን