በየደረጃው ያለው አመራር አንድነትና ወንድማማችነት በማጠናከር የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ተጠየቀ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 09/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በየደረጃው ያለው አመራር አንድነትና ወንድማማችነት በማጠናከር የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ በምክትል ርዕስ መስተዳድር ማዕረግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፋይናንስ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተፈሪ አባተ አስገነዘቡ።
በጎፋ ዞን የገዜ ጎፋ ወረዳ እና ቡልቂ ከተማ አሰተዳደር ተወላጆች ምሁራን አንድነት እና ወንድማማችነት ማጠናከሪያ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
በጎፋ ዞን የቡልቂ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ኢንጂነር ተመስገን ጣሰውና የገዜ ጎፋ ወረዳ ዋና አሰተዳደሪ አቶ አብርሃም ብርሃኑ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት፤ መድረኩ የአካባቢ ተወላጆች በአካባቢ ሠላም፣ ልማት እና አንድነት ላይ ያላቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ ያለመ መሆኑን ተናግረዋል።
አቶ ተፈሪ አባተ በምክክር መድረኩ እንዳሉት፤ በአካባቢው ተወላጆች መካከል የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት በመፍጠር ወንድማማችነትን ይበልጥ ለማጠናከር አሰፈላጊ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
በየደረጃው ያለው አመራር ከመጠላለፍና ከመገፋፋት አስከፊ የፖለቲካ አዙሪት በመላቀቅ አንድነትና ወንድማማችነት በማጠናከር የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ አሳስበዋል።
የቡልቂ ከተማ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀይሉ ባበና፤ በአካባቢው የተሰሩ መሠረተ ልማቶች የተፈጥሮ ሀብት አጠቃቀም ዙሪያ ሰነድ አቅርበው ውይይት እየተደረገ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ መላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
“አንድነታችንን በማጎልበት የህዝብ ጥቅም የሚያስቀድም ፖለቲካ ማራመድ ይጠበቅብናል” ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ
የሕብረ-ብሔራዊ አንድነት መጠናከር መሰረት የሆነው ብዝሃነትን በአግባቡ የማስተናገድ ሂደት ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው መሆኑ ተገለፀ
በክረምቱ ወራት ሊከሰቱ የሚችሉ የተለያዩ አደጋዎችን ለመከላከል አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ