በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የከተማ ልማትና ኢንዱስትሪ ክላስተር አስተባባሪና የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ስንታየሁ ወልደሚካኤል የከተማ ልማት ስራዎችን ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በተለይም በኮሪደር ልማት፣ በመሠረተ ልማት፣ በማህበር ቤት ልማት፣ በኢንዱስትሪ ዞን መሬት ማካለልና ማልማት ስራዎች ላይ የተሻለ አፈፃፀም ተመልክተናል ብለዋል።
እስካሁን ያልተጀመረው የአንድ ከተማ አንድ ፕሮጀክት ስራ በአስቸኳይ እንዲሰራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡
ለአቅመ ደካማ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገንብቶ የተላለፈው የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ የሚበረታታና ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል ሲሉም ጠቁመዋል ።
በግንባታ ደረጃ የተያዘው የኮሪደር ልማት ዕቅድ አነስተኛና እንዲጠናቀቅ ከተያዘው ጊዜ አንጻር አፈጻጸሙ ዝቅተኛ በመሆኑ ፍጥነትን ይጠይቃል ብለዋል፡፡
የክላስተር ቢሮው ግንባታ ከሌሎች ሳይቶች አንጻር የተጓተተ በመሆኑ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ግብረ መልስ ተሰጥቶበታል፡፡
ዘጋቢ፤ ባዬ በልስቲ

More Stories
ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ለጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላለፉ
ለአፍሪካ ተምሳሌት ከሆነ ምርጫ ወደ መንግሥት ምስረታ!
ትልቅ ሀገር፣ ትልቅ ህዝብ፤ ታላቅ ርዕይ