በየም ብሔረሰብ የባህላዊ መድኃኒት ለቀማና ቅመማ ጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ በሳጃ ከተማ እየተካሄደ ነው
በየም ብሔረሰብ የባህላዊ መድኃኒት ለቀማና ቅመማ ጥናት ውጤት ላይ ያተኮረ የግምገማ መድረክ “ሀገር በቀል ዕውቀቶች እና ባህላዊ እሴቶች ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ቃል በሳጃ ከተማ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት እየተካሄደ ይገኛል።
የግምገማ መድረኩ የኢፌዲሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በመተባበር ያዘጋጁት ስለመሆኑም ተመላክቷል።
በመድረኩ ላይ የኢፌዲሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ነፊሳ አብዱልማዲ፣ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ብሄረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አቡቶ አኒቶ እና የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉን ጨምሮ የክልል እና የዞን ክፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ማሙዬ ፊጣ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ23ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛና በማታ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 347 ተማሪዎችን አስመረቀ
በ2018 በጀት ዓመት የተቀመጡ ግቦችን በማሳካት የህዝቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል – አቶ ፍቅሬ አማን
ሚዲያን ለአዎንታዊ ነገር በመጠቀም ወጣቱ ሀገርን መገንባት አለበት – የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን