የወረዳው የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ብሩክ በላይነህ በወረዳው ለሶስተኛ ዙር በማህበር ለተደራጁ ስራ ፈላጊ ወጣቶች ኮርማ፣ በግና ፍየል፣ ቅቤ እንዲሁም እህል ከ3 ሚሊዮን 300 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጭ ግዢ በመፈጸም ስርጭት ተደርጓል ነው ያሉት ፡፡
የስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ምክትልና የገጠር ስራ ዕድል ፈጠራ ዘርፍ ኃላፊ ወይዘሮ ገነት ኃ/ማርያም በበኩላቸው፤ በተያዘው በጀት ዓመት በ5 ቀበሌ ለ462 ወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ግብ ተጥሎ በዚህም ከዕቅዱ አንጻር መቶ በመቶ ማሳካት መቻሉንም አስረድተዋል።
ለወጣቶች ተጨማሪ ድጋፍ ፕሮጀክት በህይወት ክህሎት ስልጠና እና በስብዕና ግንባታ እንዲሁም ኮርማ፣ በግና ፍየል፣ ቅቤ፣ ዶሮ እና እህል ግዢ በመፈጸም ለኢንተርፕራይዞች በማቅረብ አብረው እየሰሩ እንዳሉ የተናገሩት ወይዘሮ ገነት ከ3 ሚሊዮን 300 ሺህ ብር በላይ በሆነ ወጭ በዚህ ፕሮጀክት ታቅፈው ለሚገኙ 5 ቀበሌዎች ለ33 ኢንተርፕራይዞች ግዢ ፈጽሞ ስርጭት እያደረገ እንደሚገኝም ገልጿል።
በቦታው አግኝተን ካነጋገርናቸው ተጠቃሚ ወጣቶች መካከል በዛብሽ ባንጫ፣ ታገሰ ጎዳንች እና ጌታሁን አይናቶ በሰጡት አስተያየትም የአደይ ፕሮጀክት ከወረዳው ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ጋር በመሆን የተለያዩ የክህሎት ስልጠናና ኮርማ፣ በግና ፍየል፣ ቅቤ፣ ዶሮ እና እህል ግዢ በመፈጸም ስርጭት እያደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል።
ወጣቶች ከስራ ጠባቂነት ወደ ስራ ፈጣሪነት በመሸጋገራቸው ኑሯቸውን ለማሻሻል የተሻለ ዕድል እንደሰጣቸው ተናግረዋል።
ዘጋቢ ፡ አንዱአለም ኡማ – ከዋካ ቅርንጫፍ
More Stories
የወላይታ ዞን “ሁለንተናዊ የሴቶች ተሳትፎ ለጋራ ብልፅግና” በሚል ሀሳብ የተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዞናዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ
“ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴንም እወጣለሁ”በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ክልል አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ልማት በማፋጠን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሻሻል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገለፀ