የጠምባሮ ልማት ማህበር የሀዋሳ ዙሪያ ማስተባበሪያ በይፋ ተመሰረተ
ልማት ማህበሩ ግንቦት 9 ቀን 2016 ዓ.ም በይፋ ከተመሰረተ በኋላ አዲስ አበባና ሀደሮ ከተማ ቅርንጫፎች በመክፈት ስራዎች እየሰራ ነው።
ከኢፌድሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ፈቃድ ወስዶ ስራውን የጀመረው የጠምባሮ ልማት ማህበር የተለያዩ የልማት ስራዎችን ለመስራት ዓላማ ይዞ በአዋጅ የተቋቋመ ነው።
ማህበሩ በትምርት፣ በጤና፣ በመሰረተ ልማት፣ በግብርናና አካባቢ ጥበቃ አንዲሁም በስራ ዕድል ፈጠራ ስራዎችን ለመስራት እንቅስቃሴ ጀምሯል።
ዛሬ ላይም በሀዋሳና አካባቢው ከሚኖሩ የብሄረሰቡ ተወላጆች ጋር በቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ በሀዋሳ ከተማ ውይይት ተደርጓል።
ዘጋቢ፡- ባዬ በልስቲ

More Stories
የቡርጂ ዞን ምክር ቤት አቶ ትንሳኤ ዮሐንስ ወጌ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾመ
የወባ በሽታ ስርጭትን የመከላከልና የመቆጣጠርን ጉዳይ ቀዳሚ ተግባር አድርጎ እየሰራ መሆኑን የስልጤ ዞን ጤና መምሪያ አስታወቀ
አገልግሎት አሰጣጡን በማዘመን ተገልጋዩን ለማርካት እየሰራ መሆኑን የአርባ ምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል አስታወቀ