በሁሉም ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሴቶች የልማት ህብረትንና የስትሪንግ ኮሚቴ እንቅስቃሴን ይበልጥ ሊጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ
ሀዋሳ፡ ሰኔ 01/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በኢኮኖሚ፣ ማህበራዊና በፓለቲካው ዘርፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት ለማሳደግ የሴቶች የልማት ህብረትንና የስትሪንግ ኮሚቴ እንቅስቃሴን በይበልጥ ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ።
ይህም የተገለጸው የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ቢሮ “የሴቶች የልማት ህብረቶች ለክልላችን ኢኒሼቲቮች ያላቸው ሚና የጎላ ነው” በሚል መሪ ቃል ክልላዊ የሴቶች የልማት ህብረት የስትሪንግ ኮሚቴ የንቅናቄና የውይይት መድረክ በአርባምንጭ ከተማ በተከናወነበት ወቅት ነው።
የሴቶችን የልማት ህብረት ማጠናከር ቤተሰብን አከባቢንና ሀገርን ማጠናከር ነው የሚሉት ተሳታፊዎቹ የሴቶች የልማት ህብረትን በይበልጥ ከተጠቀምን ዘርፈ ብዙ ችግር የምንፈታበትና የተለያዩ ኢኒሼቲቮችን የምናሳልጥበት ነው ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
በተለይ በሴቶች ልማት ህብረት የሚታዩ ውስንነቶችን ከመቅረፍ ረገድ የመስሪያና የመሸጫ እንዲሁም የገበያ ትስስርን በማጠናከር የሴቶችን ተጠቃማነት በይበልጥ ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል አስተያየት ሰጪዎቹ።
የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊ አቶ እንደሻው ሽብሩ የሴቷን የልማት ህብረት ማጠናከር የሴቷን ጤና በይበልጥ ለመጠበቅና የጤና ፓሊሲውን ለማሳካት የሚያግዝ በመሆኑ ህብረቱን ማገዝና ማጠናከር ያስፈልጋል ብለዋል።
የክልሉ ሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ካሰች ኤልያስ እንዳሉት የሴቶች የልማት ህብረት ላይ እያንዳንዷ ሴት ተጠቃሚ እንድትሆን ለሴቶች ትኩረት ሰጥተን ልንሰራ ይገባል።
የስትሪንግ ኮሚቴውን በማጠናከር በትምህርት፣ በጤናና በግብርናው ዘርፍ የሴቷን ተጠቃሚነት ባረጋገጠ መልኩ መስራት ይገባል የሚሉት ወ/ሮ ካሰች እናቶች በቴክኖሎጂው ረገድ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በቀጣይ ወርደን መስራት ይገባናል ብለዋል።
ከመስሪያና መሸጫ ቦታ እንዲሁም ከገበያ ትስስር ጋር የሚነሱ ውስንነቶችን ለመቅረፍ ሁሉም በባለቤትነት ሀላፊነቱን ሊወጣ ይገባል ሲሉ አጠቃለዋል።
የክልሉ የመንግስት ረዳት ተጠሪ አቶ ንጋቱ ዳንሳ በማጠቃለያ ሀሳባቸው እንደገለጹት የሴቶች ልማት ህብረት አደረጃጀት ብቻውን ግብ ስላልሆነ የሴቷን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የስትሪንግ ኮሚቴውን ተግባር ማጠናከር አማራጭ የሌለው ተግባር ነው ብለዋል።
የተለያዩ ኢኒሼቲቮች ለማሳካት የሴቶች ልማት ህብረት አማራጭ የሌለው በመሆኑ ህብረቱን ማገዝና ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸው ለሚሰሩ ሴቶች ከመሬት አቅርቦትና ከመሰል ችግሮች ጋር የሚነሱ ውስንነቶችን በፍጥነት በመቅረፍ የሴቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል ሲሉ ገልጸዋል።
የሴቷን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጠናከር ቅንጅታዊ ስራ እንደሚያስፈልግ የገለጹት አቶ ንጋቱ ወደ ምርት ማምረት የገቡ ሴቶችን ተሞክሮ በማስፋት ሌሎች አምራቾችን መፍጠር እንደሚያስፈልግ በማጠቃለያቸው አንስተዋል።
ዘጋቢ: ማርታ ሙሉጌታ – ከአርባ ምንጭ ጣቢያችን
More Stories
የወላይታ ዞን “ሁለንተናዊ የሴቶች ተሳትፎ ለጋራ ብልፅግና” በሚል ሀሳብ የተፅዕኖ ፈጣሪ ሴቶች ዞናዊ የውይይት መድረክ ተካሄደ
“ሀገሬን እገነባለሁ ኃላፊነቴንም እወጣለሁ”በሚል መሪ ቃል የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶች ክልል አቀፍ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል
የጉንችሬ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ልማት በማፋጠን የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት ለማሻሻል ጥረት እያደረገ እንደሚገኝ ገለፀ