የጥበብ ባለሙያዎች ሀገር ችግር ውስጥ ስትገባ ቀድመው የሚደርሱ ናቸው- አቶ በየነ በራሳ
“ሀገር ለጥበብ፣ ጥበብ ለሀገር ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል ለኪነ ጥበብ ባለሙያዎች የተዘጋጀ የውይይት መድረክ በሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ተካሄዷል ፡፡
በመድረኩም የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንትና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በየነ በራሳ፣ የክልሉ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ እንዲሁም ከ4ቱም ዞኖችና ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
የክልሉ ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃጎ አገኘሁ በመክፈቻ ንግግራቸው፤ በለውጡ መንግስት እንደሀገር የተመዘገቡ ጠንካራ ጎኖችን ለማስቀጠልና መፈታት ያለባቸው ድክመቶችን በጋራ ተነጋግሮ ለመፍታት ያለመ ምክክር ነው ብለዋል ፡፡
በሲዳማ ክልል የተካሄደው ክልል አቀፍ ሀገራዊ ምክክር መንግስት ለጥበብ ዘርፍ ትኩረት በመስጠት በክልሉ ከ4ሺህ በላይ የኪነጥበብ ባለሙያዎችን እንዲሳተፉ ሁኔታዎችን ማመቻቸቱን አመላክተዋል ፡፡
በክልሉ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች በቂ ትኩረት እንዳልተሰጣቸው፤ ለጥበብ ባለሙያዎች ማህበር ቢቋቋም፣ በጥበቡ ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች ሰርተው ራሳቸውን የሚችሉበት መንገድ ቢመቻች፣ ከታች የሚመጡ ታዳጊዎች ኪነ ጥበብ የሚሰለጥኑበት አዳራሾች ቢመቻቹ የሚሉ ሀሳቦች በተሳታፊዎች ተነስተዋል፡፡
ለሀገራችን አርት እድገት ዋጋ ለከፈሉ አርቲስትች ትኩረት በመስጠት ጥበቡ በሚፈለገው ልክ እንዲሄድ የክልሉ መንግስት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ አመላክተዋል።
የሲዳማ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንትና የትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በየነ በራሳ ኪነጥበብ ለሀገር ያለው ፋይዳ ትልቅ እንደሆነ ጠቁመው ለባለሙያዎች እውቅና እንደሚሰጣቸውና የኪነጥበቡ ባለሙያዎች ደግሞ ጠንካራ ማህበር እንዲፈጠር መትጋት እንዳለባቸው አስገንዝበው የተነሱ ጥያቄዎች ተገቢ በመሆናቸው ደረጃ በደረጃ እንደሚመለስ ገልጸዋል።
የጥበብ ባለሙያዎች ሀገር ችግር ውስጥ ስትገባ ቀድመው የሚደርሱ ናቸው ብለው ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ መንግስት ከማንኛውም ጊዜ በተሻለ መልኩ ከጥበብ ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት ለመስራት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል ፡፡
ዘጋቢ፡ ሐና በቀለ
More Stories
እመርታ ለዘላቂ ከፍታ!
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ የእምርታ ቀንን በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት:-
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ/ር) መልዕክት፡-