በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ የተለያዩ የመሠረተ ልማቶች የምረቃ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል

በጉራጌ ዞን እኖር ኤነር መገር ወረዳ የተለያዩ የመሠረተ ልማቶች የምረቃ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል

በወረዳው የምረቃ ስነ-ስርዓት እየተከናወነባቸው ከሚገኙ መሠረተ ልማቶች መካከል የወረዳው አስተዳደር ባለአራት ወለል ህንፃ እና የወረዳው ፍርድ ቤት ህንፃ ይገኙበታል።

የእኖር ኤነር መገር ወረዳ አስተዳደር ከ104 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርጎ ያስገነባቸው ፕሮጀክቶችን አስመርቆ ለአገልግሎት ክፍት በማድረግ ላይ ይገኛል።

በተጨማሪም በወረዳው የገጠር ኮሪደር ልማት እንቅስቃሴ የደረሰበት ደረጃ የመስክ ምልከታ ተደርጓል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀልን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር የስራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጥሪ የተደረገላቸው የአካባቢው ተወላጆችና ባለሀብቶች እንዲሁም የአካባቢው ነዋሪዎች በመታደም ላይ ናቸው።

ዘጋቢ፡ ሪድዋን ሰፋ – ከወልቂጤ ጣቢያችን