በጉራጌ ዞን ጌታ ወረዳ የተለያዩ የመሠረተ ልማት ስራዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት እየተካሄደ ይገኛል
በወረዳው የምረቃ ስነ-ስርዓት እየተካሄደባቸው ከሚገኙ መሠረተ ልማት ስራዎች መካከል የመንገድ መሰረተ ልማት፣ የወረዳው ጤና ጽህፈት ቤት ግንባታ እና የቋንጤ የማህበረሰብ መድኃት ቤት እንዲሁም ከ100 ሚሊየን ብር በላይ የሚፈጀው ጌታ ወረዳ የባህል አዳራሽ ግንባታ መሰረተ ድንጋይ የማኖር ስነ-ስርዓት በመርሃ ግብሩ መሰረት እየተካሄደ ይገኛል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱ ላይ የጉራጌ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ላጫ ጋሩማ፣ የብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አለማየሁ ገ/መስቀልን ጨምሮ የክልልና የዞን የስራ ሀላፊዎች፣ ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ጥሪ የተደረገላቸው የአካባቢ ተወላጆችና ባለሀብቶች እዲሁም የአካባቢ ነዋሪዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ተዘራ በቀለ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ