በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ቀቤና ልዩ ወረዳ ሁለተኛ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ በዛሬዉ እለት መሰጠት ተጀምሯል።
በልዩ ወረዳዉ ከ17 ሺህ በላይ ህጻናት ክትባቱን እንደሚወስዱ የቀቤና ልዩ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ገልጿል።
በልዩ ወረዳዉ ከዛሬ ግንቦት 22 ጀምሮ ለተከታታይ አራት ቀናት ቤት ለቤት ለሚሰጠዉ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ የክልሉ ጤና ቢሮ ሀላፊዎችን ጨምሮ በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነዉ የተጀመረዉ።
ከፖሊዮ ክትባት ጎንለጎን የላንቃ መሰንጠቅ፣ ቆልማም እግር ልየታ ፣የፌስቱላ ህመም ተጠቂ ልየታ እና ሌሎችም የጤና ነክ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተደርጎ ይሰራልም ተብሏል።
በልዩ ወረዳዉ በመጀመሪያ ዙር የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ከ13 ሺህ በላይ ህጻናት መከተባቸዉ ሲታወስ በሁለተኛዉ ዙር ከ17 ሺህ በላይ ህጻናት የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሆናሉ።
ዘጋቢ፡- ሪያድ ሙህዲን

More Stories
በኮሬ ዞን የአስፈጻሚ መሥሪያ ቤቶች መልሶ የማደራጀት ምክክር መድረክ ተካሄደ
በአጋር ድርጅቶች የሚተገበሩ ፕሮጀክቶች የመንግስት የልማት ክፍተት በመሙላት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በሌማት ትሩፋት ከቤት ፍጆታ ባለፈ ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚ መሆናቸውን የምዕራብ አባያ ወረዳ አርሶ አደሮች ገለፁ