ሀገራችን በአህጉርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምትታወቅባቸው በርካታ እሴቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የአሁኑ ትውልድ ሀላፊነት እንዳለበት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ አስገነዘበ
ዩኒቨርሲቲው የሀገር በቀል ቋንቋና ባህልን ለማጎልበት ያለመ ስልጠና ለሚዲያ ባለሙያዎች እየሰጠ ይገኛል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሀብቴ ዱላ ባስተላለፉት መልዕክት፤ ኢትዮጵያ በአህጉርም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የምትታወቅባቸው የበርካታ እሴቶች ባለቤት ናት ብለዋል።
በመሆኑም እነዚህ እሴቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የአሁኑ ትውልድ ሀላፊነት እንዳለበትም አመላክተዋል።
በስልጠና መድረኩ የሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ ረድኤት እግዜሩ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የተገኘው አንፃራዊ ሰላም የእርስ በርስ ግንኙነቶችን ከማጠናከር ባለፈ ለረጅም አመታት በፀጥታ ችግር ያለማውን የማዕድን ሀብት በመጠቀም የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በማጂ ወረዳ የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ
በአካል ጉዳተኝነት ተስፋ ባለመቁረጥ የተገኘ ስኬት
ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ