በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ የ2017 ዓ.ም የጎልማሶች ትምህርት የብርሃን ምዘናን በ1 መቶ 12 ጣቢያዎች አካሂዷል
የማንበብና የመፃፍ ችግርን ለመቅረፍ የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት የላቀ ሚና እንዳለው በምዘናው የተሳተፉ ጎልማሶች ገልፀዋል።
የጎልማሶችና መደበኛ ያልሆኑ የትምህርት ዘርፍ የትምህርት ብርሃን ምዘናው የማንበብ፣ የመፃፍና የማስላት ችግራቸውን እንደቀረፈላቸው በምዘናው ወቅት ካነጋገርናቸው ጎልማሶች መካከል አቶ ደምሴ መንገሻ እና ወይዘሮ ካሰች አየለ ገልፀዋል።
በኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ የጎልማሶች ትምህርት ዳይሬክተር ወይዘሮ ማስረሻ ሙላት፤ የትምህርት ብርሃን ምዘና ዓላማን ገልፀው ለዘርፉ ውጤታማነት የባለድርሻ አካላት ተሳትፎና ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑን አስረድተዋል።
የኣሪ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ ዳግም መኮንን፤ በኢትዮጵያ መደበኛ ትምህርት ረጅም ታሪክ እንዳለው ተናግረው መደበኛ ያልሆነ የተቀናጀ የጎልማሶች ትምህርት መደበኛውን በማገዝ መሀይምነትን ለማስወገድ ታልሞ የተዘጋጀ የትምህርት ለሁሉም ስትራቴጅክ አንዱ አካል ተድርጎ እየተሠራ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በዞኑ 1323 ወንድ 1643 ሴት በአጠቃላይ 2966 ጎልማሶች በ1 መቶ 12 ጣቢያዎች የብርሃን ምዘናውን መቀበላቸውን ኃላፊው ገልፀው፤ የጎልማሶች ትምህርትን ለማጠናከር ከአመለካከት ጀምሮ ያሉ በርካታ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍ እየተሠራ እንዳለም አስረድተዋል።
ዘጋቢ፡ ተመስገን አሰፋ – ከጂንካ ጣቢያችን

More Stories
በክረምት ወራት የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ወጣቶች አልባሌ ስፍራ እንዳይውሉ ከማድረግ በተጓዳኝ ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ምቹ እድል እየፈጠረ መሆኑ ተገለጸ
በአርሰናል እንደ አዲስ ብርሃን የፈነጠቀው ክርስቶስ ጾሊስ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የጂንካ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ23ኛ ዙር በተለያዩ የሙያ መስኮች በመደበኛና በማታ መርሃ ግብር ያሰለጠናቸውን 347 ተማሪዎችን አስመረቀ