ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ጎፋ ዞን ገባ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) ታላቁ የህዳሴ ግድብ ዋንጫ ወደ ጎፋ ዞን ስገባ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች አቀባበል አድርገዋል።
ዋንጫው በጋሞ ዞን የነበረውን የቆይታ ጊዜው አጠናቆ ወደ ጎፋ ዞን በክልልና በጋሞ ዞን ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች አሸኛኘት ተደርጎለታል ።
ወደ ጎፋ ዞን ሲገባ የዞን ፣ የወረዳና የከተማ አስተዳደር ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የአከባቢው ነዋሪዎች ማዜ ወንዝ ጀምሮ አቀባበል እየተደረገ ይገኛል።
ዘጋቢ፡ አይናለም ሰለሞን – ከሳውላ ጣቢያችን
More Stories
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ እያስመዘገበች ላለችው የዕድገት ጉዞ ቀጣይነት የትምህርት ተቋማት ሚና ከፍተኛ በመሆኑ ለትምህርት ጥራት በቁርጠኝነት ሊሰሩ ይገባል ሲል የጋሞ ዞን አስተዳደር አሳሰበ
በትምህርት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን አጽንቶ ማስቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ገለፁ
በኮንታ ዞን ጳጉሜን 1 – የጽናት ቀን በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል