የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ የፌደራልና የክልሎች ልዑክ በሀላባ ዞን የመስክ ምልከታ እያደረገ ነው
ሀዋሳ፡ ግንቦት 20/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ቢሮ፣ የፌደራልና የክልሎች ልዑክ በሀላባ ዞን የተሰሩ የልማት ስራዎችን ምልከታ እያደረገ ነው።
ሶስተኛ ቀኑን የያዘው የሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም የሀረሪና የጋምቤላ ክልል ሴቶች ህፃናት ቢሮ አመራሮችና ባለሙያዎች ጉብኝት በሀላባ ዞን በሴቶች ህብረት ማህበራት እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን እየተመለከተ ነው።
በዞኑ ዌራጂዶ ወረዳ ሲምቢጣ ቀበሌ የለማ የፍራፍሬና አትክልት ልማት ስራን ተመልክተዋል።
በዞኑ ሴቶች ህብረት ማህበራት እየተሰሩ ያሉ የግብርና ስራዎችን ተዘዋውረው በመጎብኘት ላይ ናቸው፡፡
ዘጋቢ፡ ባዬ በልስቲ

More Stories
የተገኘው አንፃራዊ ሰላም የእርስ በርስ ግንኙነቶችን ከማጠናከር ባለፈ ለረጅም አመታት በፀጥታ ችግር ያለማውን የማዕድን ሀብት በመጠቀም የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በማጂ ወረዳ የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ
በአካል ጉዳተኝነት ተስፋ ባለመቁረጥ የተገኘ ስኬት
ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ