በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ ቡድን የ2017 በጀት አመት አስር ወራት የስራ እንቅስቃሴን በጉራጌ ዞንና በወልቂጤ ሳታላይት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምልከታ እያደረገ ነው
ሀዋሳ፡ ግንቦት 19/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በስራና ክህሎት ሚኒስቴር የስራ ክህሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሰለሞን ሶካ የተመራ ቡድን የ2017 በጀት አመት አስር ወራት የስራ እንቅስቃሴ የክህሎት ልማት፣ በስራ ዕድል ፈጠራ እና በስራ ላይ ደህንነት እንዲሁም በተቋም ግንባታ ዙሪያ በጉራጌ ዞንና በወልቂጤ ሳተላይት ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ምልከታ እያደረገ ነው።
በዞኑ በመስኖ ልማት በበልግና በመኸር ሰብልና በከብት እርባታ የተሰሩ ስራዎች ጉብኝት የተደረገ ሲሆን ኢንተርፕራይዞች በአመት ሶስት ጊዜ በማምረትና በተሰማሩባቸው ዘርፎች ውጤታማ መሆን ከተቻለ ሰፋፊ ማሳዎችን በማልማት ወደ ኢንቨስትመንት ማደግ እንደሚቻል በጉብኝቱ ተገልጿል::
የወልቂጤ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፕሮጀክቶች ጋር በመቀናጀት እየሰጠ ያለው ክህሎት ነክ ስልጠና እና የውስጥ ገቢን ለማሳደግ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችንም ተመልክተዋል።
በጉብኝቱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ ሀላፊ ሙስጠፋ ኢሳን ጨምሮ የክልልና የዞን አመራሮች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፡ ሄኖክ ተክሌ – ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
የተገኘው አንፃራዊ ሰላም የእርስ በርስ ግንኙነቶችን ከማጠናከር ባለፈ ለረጅም አመታት በፀጥታ ችግር ያለማውን የማዕድን ሀብት በመጠቀም የአካባቢውን ኢኮኖሚ ለማነቃቃት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው በማጂ ወረዳ የሚገኙ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ
በአካል ጉዳተኝነት ተስፋ ባለመቁረጥ የተገኘ ስኬት
ከ98 ሚሊዮን ብር በላይ የውስጥ ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ