የሰላምና የልማት ፎረም መካሄድ በሕዝቦች መካከል የጋራ መቀራረብና አብሮ የመልማት ዕድልን በማስፋት ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ያግዛል – ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
ሀዋሳ፡ ግንቦት 17/20017 ዓ.ም (ደሬቴድ) የሰላምና የልማት ፎረም መካሄድ በሕዝቦች መካከል የጋራ መቀራረብና አብሮ የመልማት ዕድልን በማስፋት ዘላቂ ሠላምን ለማረጋገጥ ያግዛል ሲሉ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናገሩ፡፡
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልልዊ መንግሥትና የጋምቤላ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የጋራ የሠላምና የልማት ትብብር ፎረም እየተካሄደ ነው፡፡
ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ባስተላለፉት መልዕክት በ2016 ዓ.ም በይፋ ፍረሙ ከተደረጀ ወዲህ በሁለቱ የክልል መንግሥታት የሠላም፣ የልማት፣ የትብብርና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ስራዎች ተጠናክረው መሰራታቸውን ተናግረዋል ፡፡
በሁለቱ ክልሎች አጎራባች አካባቢዎች የሚከሰቱ የጸጥታ ስጋቶችን በጋራ መከላከል፣ ችግሮች ሲከሰቱም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ፈጥኖ የእርምት እርምጃ የመውሰድ ተግባራት ተጠናክረው መሰራታቸውን ገልጸዋል ፡፡
የኮንትሮባንድና ሌሎች የወንጀል ድርጊት ጠቋሚ ክስተቶች በሚያጋጥሙበት ወቅትም የተቀናጀ የጋራ ምላሽ መስጠት የሚያስችሉ ተግባራትን በመፈጸም የወንጀል ክስተቶች እንዲቀንሱ ማድረግ ተችሏልም ሲሉ ተናግረዋል ፡፡
በሕዝቦች መካከል የጋራ መቀራረብና አብሮ የመልማት እድል እንዲሰፋ ትኩረት በመስጠት የዘላቂ ሠላም ግንባታ ሥራችን እንዲሳለጥ ሁለቱ ክልሎች ከፌዴራል የጸጥታና ደህንነት አካላትና ከሠላም ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሚገኝም ርዕሰ መስተዳድር ደክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ ተናግረዋል ፡፡
ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሂደው ይህ የጋራ የምክክር መድረክ በአንደኛ ዙር የጋራ ፎረም የተቀመጡ አንኳር ተግባራት አፈጻጸም ያለበት ደረጃን የሚገመገምበት መሆኑንም አንስተዋል ፡፡
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ወ/ሮ አለሚቱ ኦሞድ ባስተለለፉት መልዕክት በሁለቱ ክልሎች ዘመን የተሻገረ አንድነት፣ ወንድማማችነትና እህትማማችነትን ይበልጥ ማጠናከርና ማስቀጠል ይገባናል ሲሉም ተናግረዋል ፡፡
በሰላምና ልማት ፎረም በተሰራው ስራም ባህል፣ ቋንቋእና ቦታ ሳይገድባቸው በማህበራዊና ኢኮኖሚዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የሁለቱ ክልል ህዝቦች በነጻነት እየሰሩና ተጠቃሚ እየሆኑ መምጣታቸውን ወ/ሮ አለሚቱ ተናግረዋል ፡፡
ክልሎቹ ዕምቅ የተፈጥሮ ጸጋ ያሏቸው በመሆኑ ከክልሉ አልፎ ለሀገር የሚጠቅሙ በመሆናቸው በክልሎቹ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚስተዋሉ ግጭቶችን በዘላቂነት በመቅረፍ ህዝቦችን ዘላቂ የሰላምና የልማት ተጠቃሚነትን ማረጋገጥ ይጠበቅብናል ሲሉም ወ/ሮ አለሚቱ ተናግረዋል ፡፡
የሰላም ሚኒሰቴር ሚንስትር አቶ መሀመድ እድሪስ በበኩላቸው ባስተላለፉት መልዕክት ዘላቂ ሰላምንና ልማትን ለማስቀጠል የአመራር ቁርጠኝነትን ማጠናከር ይገባል ብለዋል ፡፡
ሁለቱ ክልሎች የጋራ ማንነት ያላቸውና በተፈጥሮ ጸጋ የታደሉ የኢትየጵያ ብልጽግና ተምሳሌቶች ናቸው ያሉት ሚኒስትሩ ጸጋዎችን ወደ ዕድል በመለወጥ ህዝቦች ተተቃሚነትን ማረጋገጥ እንደሚገባ ጠቁመው፥ በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ ተከስቶ የነበረውን ግጭት በማስቀረት ማህበረሰቡ የራሳቸውን ባህላዊ እሴት በመጠቀም ችግሮችን መቅረፍ በመቻላቸው በኢፌድሪ መንግስት ስም አመስግነዋል፡፡
ዘጋቢ፡ አብዮት በቀለ – ከሚዛን ጣቢያችን
More Stories
የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ መቆርቆር ቀበሌ ያስገነባው የንጹህ መጠ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
የኡዱሂያ የዕርድ ስርዓት….የአብሮነት ነፀብራቅ
በቅርቡ በሚሰጠው የ6ኛ እና የ8ኛ ክልላዊ ፈተና ላይ ከ53 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀርቡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ትምህርት መመሪያ አስታወቀ