በኮንታ ዞን የሽግግር ም/ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 26ኛው መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
ጉባኤውን በንግግር የከፈቱት የዞኑ መ/ቤት ዋና አፌ ጉባኤ አቶ ብርሃኑ አቱሞ ም/ቤት የዞኑ መንግስት ከፍተኛ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት በመሆኑ መንግሥታዊ ዕለት ተዕለት ሥራችን ሲከናወን የዜጎች መብቶችና ነፃነቶች መከበርና መልካም አስተዳደር መስፈኑን የማረጋገጥ ሥራዎችን ሲሠራ መቆየቱን ተናግረዋል።
በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶች መመዝገባቸውን ተናግረው ለዘመናት የመልካም አስተዳደር ችግር ሆነው የቆዩ የመሠረተ ልማት ጥያቄዎችን በመመለስ የህዝብ ተጠቃሚነትን የማረጋገጥ ሥራ መሠራቱን አቶ ብርሃኑ ገልፀዋል።
ጉባኤው ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲሆን የ2018 በጀት ዓመት ዓመታዊ የአስፈፃሚ መስሪያ ቤት ማጠቃለያ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት፣ የ2019 በጀት ዓመት ጠቋሚ ዕቅድና ረቂቀ በጀት ቀርቦ ተወያይቶበት እንደሚያፀድቅ ከወጣው መረሃ ግብር ማወቅ ተችሏል።
ዘጋቢ፡ ብርሃኑ ግንባቶ – ከዋካ ጣቢያችን

More Stories
ጥራቱ የተጠበቀ ከ500 ቶን በላይ እሸት ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሠራ መሆኑ ተገለጸ
አዲሱ የካቢኔ ስብጥር ኢትዮጵያ የሁሉም መሆኗን በተግባር ያሳየ ነው – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)
ዕጩ የካቢኔ አባላት ከወትሮ በተለየ መንገድ ባለዕዳና ከፍተኛ አደራ የተጣለባቸው መሆኑን እንዲገነዘቡ ማሳሰብ እወዳለሁ – ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)