በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቻችን የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተጠናከረ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ የኢፌዲሪ ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ
23ኛው አለም አቀፍ ሲምፖዚየም “የውሀ ሀብት ለዘላቂ ልማትና ተጠቃሚነት” በሚል መሪ ቃል በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።
በአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ትብብር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ተክሉ ወጋየሁ፤ የሲምፖዚየሙ መዘጋጀት የውሀ ሀብትን በዘላቂነት ለመጠቀም እንዲያስችል የዘርፉ ምሁራን ሀሳባቸውን፣ ፈጠራቸውንና ተሞክሯቸውን እንዲያጋሩ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁመዋል።
ለፖሊሲ አውጭዎችና ለሚዲያ ባለሙያዎች ለሀገራችን የውሀ ሀብት አጠቃቀም የሚሻለውን በመለየት መጠቀም የሚያስችል እውቀት የሚያስጨብጥ ነውም ብለዋል።
መሰል ሲምፖዚየሞች ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ወንዞችን ለመጠቀም የሚያስችል የውሀ ዲፕሎማሲያችንን ለማጠናከር ያግዛል ሲሉ ገልጸዋል።
የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ውሀ ቴክኖሎጂ ኢንስትትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ታምሩ ተሰማ፤ በዩኒቨርሲቲው ለበርካታ አመታት የውሀ ሀብታችንን ለዘላቂ ልማት መጠቀም የሚያስችል ዘርፈ ብዙ ጥናቶች ተጠንተው ውጤት በሚያመጣ መልኩ እየተሰራ ነው፡፡ ለዚህም የዘርፉ ምሁራን ድርሻ የጎላ ነው ብለዋል።
የኢፌዲሪ ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ልዩ አማካሪ ዶ/ር ሚካኤል መሀሪ፤ ምርምርና የኢንዱስትሪ ስራዎች የሚነጣጠሉ ባለመሆናቸው የአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ በውሀ ሀብት አስተዳደርና ዘላቂ ተጠቃሚነት እንዲሁም በተፋሰስ ስራዎች ላይ እየተሰሩ ያሉ እቅዶችና እየቀረቡ ያሉ ፕሮጀክቶች በይበልጥ ሊተኮርባቸው እንደሚገባ ገልጸዋል።
በተለይ 75 ከመቶ በላይ የሚሆነው የሀገራችን ተፋሰስ ወደ ጎረቤት ሀገራት የሚፈስ በመሆኑና በጋራ የምንጠቀማቸው በመሆኑ በዲፕሎማሲው ረገድ ድንበር ተሻጋሪ ወንዞቻችንን ለመጠቀም በሚያስችለን ጉዳይ መረጃ ለአለም እንዲደርስ ከማድረግ አኳያ እየተሰሩ ያሉ ጥናቶች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለዋል።
ዘጋቢ፡ ማርታ ሙሉጌታ – ከአርባምንጭ ጣቢያችን
በድንበር ተሻጋሪ ወንዞቻችን የጋራ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተጠናከረ ስራ ሊሰራ እንደሚገባ የኢፌዲሪ ውሀና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታወቀ

More Stories
ዲግሪው “ወረቀት ብቻ ሳይሆን፣ የሀገር ተስፋና የትውልድ ኃላፊነት ነው” – አፈወርቅ ካሱ (ፕ/ር)
በክልሉ የተጀመሩ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት የሚያሳድጉ ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የድጋፍና ክትትል ስራ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የመጠጥ ውሃና ሳኒቴሽን ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ዶ/ር አስፋው ዲንጋሞ ገለጹ
የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የግብርናና ገጠር ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሀላባ ቁሊቶ ከተማ የግብርና ስራዎችን ተመለከተ