ሀዋሳ፡ ግንቦት 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በክልሉ የኦንኮ ሰርኪያሲስ እና ዝሆኔ በሽታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡን በካርተር ሴንተር ኢትዮጵያ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
እነኚህ በሽታዎች በክልሉ አብዛኞቹ አካባቢዎች ማህበራዊ ስጋትነታቸው እንደቀነሰም ተጠቁሟል።
ካርተር ሴንተር የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአለም አቀፍ ደረጃ ከ21 በላይ ለሚሆኑ አገራት በተለይ በጤናው ዘርፍ ከፍተኛ ድጋፍ ሲያደርግ እንደቆየ የማስተባበሪያ ጽህፈት ቤቱ ፕሮጀክት ማኔጀር አቶ ዮሐንስ እሸቱ ተናግረዋል።
ድርጅቱ በኢትዮጵያ ባለፉት 26 ዓመታት ከመንግሥት ጋር በመሆን የጊኒ ዎርም፣ ትራኮማ በሽታ፣ የኦንኮ ሰርኪያሲስ እና የዝሆኔ በሽታዎችን ስርጭት በመግታት እና በመቆጣጠር ረገድ ሰፊ ስራ እየሰራ ቆይቷል ብለዋል።
ይህ ተግባር የየአካባቢው ተጨባጭ ሁኔታ ላይ ተመርኩዞ እንደሚከወን የገለጹት አቶ ዮሐንስ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልልም የኦንኮ ሰርኪያሲስ እና የዝሆኔ በሽታዎችን መቆጣጠር እና ስርጭቱን ማቋረጥ ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።
የኦንኮ ሰርኪያሲስ በሽታን የመከላከል እና ስርጭቱን የማቋረጥ ስራ በክልሉ በሚገኙ ሁሉም መዋቅሮች ላይ የሚከናወን ሲሆን በዝሆኔ በሽታ መከላከል ደግሞ በ23 ወረዳዎችና የከተማ አስተዳደሮች በተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
የካርተር ሴንተር ዋንኛ አላማው በፈረንጆቹ አቆጣጠር 2030 ላይ የእነዚህን በሽታዎች ስርጭት መቆጣጠር እና ማጥፋት መሆኑን ገልጸዋል።
የኦንኮ ሰርኪያሲስ በሽታ ህክምና በመጀመሪያዎቹ 10 አመታት በአመት አንድ ጊዜ እንደሚሰጥ ጠቅሰው ከሁለተኛ ምዕራፍ በኋላ ማለትም እ.ኤ.አ 2013 ጀምሮ ደግሞ በአመት ሁለት ጊዜ እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።
በዚህም በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች እስካሁን ወደ 62 ሚሊዮን ህክምናዎችን ተደራሽ ማድረግ መቻሉን ገልጸዋል።
ይህም በየአመቱ የሚደረጉ ህክምናዎች ድምር ውጤት መሆኑን የገለጹት አቶ ዮሐንስ፤ የተደረገው እንቅስቃሴ በሽታው በአብዛኛው አካባቢዎች ላይ የማህበራዊ ስጋትነቱን እንዲቀንስ አድርጎታል ብለዋል።
በተጨማሪም በክልሉ ከሚገኙ መዋቅሮች በአስራ አምስቱ የኦንኮ ሰርኪያሲስ በሽታ ስርጭት የተቋረጠባቸዉ በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት ህክምናዉን ማቆም መቻሉን ገልጸዋል።
በተመሳሳይ የዝሆኔ በሽታን ለመቆጣጠር በተሰራው ስራ በአመት አንድ ጊዜ በሚሰጠው ህክምና በሽታው ከሚስተዋልባቸው ሃያ ሶስት መዋቅሮች አስራ ስምንቱ ላይ ከሰው ወደ ሰው የመተላለፍ ሁኔታው እንደተቀረፈም ተናግረዋል።
በተጠቀሱት አስራ ስምንት መዋቅሮች የዝሆኔ በሽታ ህክምና መቋረጡን የገለጹት አስተባባሪው፤ በአካባቢዎቹ የድህረ ህክምና ዳሰሳ ጥናት ከተሰራ በኋላ ምንም አይነት የበሽታ ምልክቶች ከሌሉ አካባቢዎቹ ከበሽታው ነጻ መሆናቸው ይረጋገጣል ብለዋል።
እነኚህ ተግባራት ውጣታማ እንዲሆኑ እና በፕሮግራሙ የሚመለከታቸው አካላት ተሳትፎ የጎላ እንዲሆን እስከ ቀበሌ ድረስ ካሉ መዋሮች ጋር በአብሮነት ይሰራል ብለዋል።
ይሁንና በግንዛቤ እጥረት የተነሳ አንዳንድ የህብረተሰብ ክፍሎች በዘመቻ የሚሰጡ መድኃኒቶችን በአግባቡ አለመውሰዳቸው እንዲሁም መድሀኒቶችን በአግባቡ ለማድረስ በሚያስቸግሩ አካባቢዎች ላይ ባለመድረሱ የበሽታዎቹን ስርጭት በሚፈለገው ልክ ለመቆጣጠር እክል መሆኑን አቶ ዮሐንስ አንስተዋል።
በመጨረሻም የአለም ጤና ድርጅት በ2030 እነኚህን በሽታዎች ከአለም ለማጥፋት የያዘውን ውጥን ከግብ ለማድረስ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ሁሉም ተባባሪ ሊሆን እንደሚገባው ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ፡ ትዕግስቱ ጴጥሮስ – ከቦንጋ ጣቢያችን
በክልሉ የኦንኮ ሰርኪያሲስና ዝሆኔ በሽታዎችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር በተሰራው ስራ ተጨባጭ ለውጥ መመዝገቡ ተገለጸ

More Stories
የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ መቆርቆር ቀበሌ ያስገነባው የንጹህ መጠ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
የኡዱሂያ የዕርድ ስርዓት….የአብሮነት ነፀብራቅ
በቅርቡ በሚሰጠው የ6ኛ እና የ8ኛ ክልላዊ ፈተና ላይ ከ53 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና እንደሚቀርቡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የሀዲያ ዞን ትምህርት መመሪያ አስታወቀ