በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን ከዞኑ ከተውጣጡ መምህራን ጋር ውይይት እየተደረገ ነው
ሀዋሳ፡ ግንቦት 16/2017 ዓ.ም (ደሬቴድ) በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የም ዞን “ትውልድ በመምህር ይቀረፃል፤ ሀገር በትምህርት ይበለፅጋል” በሚል መሪ ቃል ከዞኑ ከተውጣጡ መምህራን ጋር በሣጃ ከተማ ውይይት እየተደረገ ነው፡፡
የውይይት መድረኩ ባለፉት ጊዜያት በዞኑ በሁሉም አስተዳደር መዋቅሮች ሲካሄድ የቆየ ሲሆን በዛሬው ዕለትም የሚካሄደው ዞናዊ የማጠቃለያ ውይይት መሆኑ ተገልጿል።
የውይይቱ ዓላማም በትምህርት ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶችና እየተስተዋሉ ያሉ ጉድለቶችን እንዲሁም ቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በመለየት ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት ለመፍጠር ነው።
በውይይቱ ላይ የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ፣ የዞኑ የመንግስት ተጠሪ አቶ አብርሃም ዝናብን ጨምሮ የዞንና የወረዳ አመራሮች እንዲሁም መምህራን እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ከውይይቱ አስቀድሞ የዞኑ ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች እና ተሣታፊዎች በሣጃ ከተማ እየተሠሩ ያሉ የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል።
ዘጋቢ፡ ማሙዬ ፊጣ – ከወልቂጤ ጣቢያችን
More Stories
በትምህርት ዘርፍ የተገኙ ውጤቶችን አጽንቶ ማስቀጠል እንደሚገባ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ፀሐይ ወራሳ ገለፁ
በኮንታ ዞን ጳጉሜን 1 – የጽናት ቀን በተለያዩ ሁነቶች ተከብሯል
በዞኑ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ሠላም ወሳኝ መሆኑን የደቡብ ኦሞ ዞን አስተዳደር ገለጸ