የዉይይቱ ዋና ዓላማ በጤና ልማት ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች ይበልጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል ፣ ጉድለቶችን ደግሞ ፈጥኖ ለማረም እና በቀጣይ የተሻለ ዉጤት ለማስመዝገብ ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት መፍጠር ነዉ ተብሏል።
የየም ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሽመልስ እጅጉ እንደገለፁት ባለፉት አመታት መንግስት በጤናዉ ልማት ዘርፍ አገልግሎቱን ተደራሽ ለማድረግና ጥራቱን ከማስጠበቅ ረገድ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት የተሻለ ለውጥ መመዝገቡን ገልጸዋል።
በተጨማሪም በጤና ልማት ዘርፍ የሚስተዋሉ የደመወዝ ጭማሪ፣ የትርፍ ሰዓት ክፊያ፣ የግብዓት እጥረት እና ሌሎች የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መንግስት በአጭር፣ በመካከለኛ እና በረጅም ጊዜ ለመፍታት አቅዶ እየሰራ መሆኑም አመላክተዋል።
በዘርፉ በአፈፃፀም ረገድ የሚታዩ ጉድለቶችን ፈጥኖ ለመፍታት እየተሰራ ያለዉ ተግባር ውጤታማ እንዲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸዉን አስተዋፆ ማበርከት እንዳለባቸዉ አስተዳዳሪው ጠቅሰዋል፡፡
የየም ዞን ብልጽግና ፖርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብርሃም ዝናብ በዞኑ ያሉ ጤና ባለሙያዎች በገቡት ቃል መሠረት ቅድሚያ ለሕዝብ ጤና የሚሠሩ ናቸው ብለዋል።
የጤና ባለሙያው እያቀረበ ያለውን ትክክለኛ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠትከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየሰራን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የዞኑ ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ ሠናይ ረጉ፤ ባለሙያዎች የሚያነሱትን ጥያቄዎች ለመመለስ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተሠራ ነው ብለዋል ።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በጤናው ዘርፍ ከሚታዩ ችግሮች መካከል የደመወዝ ጭማሪ፣ የትፍ ሰዓት አገልግሎት ክፍያ ያለመከፈል፣ የተቋማት እድሣት ያለመደረግ፣ የደረጃ ዕድገት እና ዝውውር እንድሁም ከበጀት ጋር በተያያዘ የሚገጥሙ ችግሮች እንድፈቱ ጥረት መደረግ አለበት ብለዋል ።
የውይይቱ ተሳታፊዎች በክልል መንግስትና በዞን እየተሰሩ ያሉ የኮሾ ሁለገብ የፍራፍሬ መሸጫ ማዕከል ግንባታ፣ የሳጃ ከተማ ኮርደር ልማት ሥራ እንዲሁም ኢንተርፕራይዝና ማኑፋክቸርንግ ዘርፍ ሥራዎች ጉብኝት ተደርጓል።
ዘጋቢ፡- ማሙዬ ፊጣ ከወልቂጤ ጣቢያችን

More Stories
በክልሉ የሚገኙ ነዋሪዎችን ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሥራ በትኩረት እየተሠራ እንደሚገኝ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ(ዶ/ር) ገለጹ
የእናቶችንና ጨቅላ ህፃናትን ሞት ለመቀነስ በሚደረጉ ጥረቶች ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተገለፀ
የማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርእሰ መስተዳደር (ዶ/ር ) እንዳሻው ጣሰው በተገኙበት በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ የመሰረተ ልማት ፕሮጀክቶች ምርቃትና የመሰረተ ድንጋይ የማስቀመጥ ስነ-ስረዓት እየተካሄደ ይገኛል