በወላይ ዞን “ትውልድ በመምህር ይቀረጻል፣ ሀገር በትምህርት ይበለጽጋል” በሚል መሪ ቃል ዞናዊ የመምህራን ውይይት መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊና የመማር ማስተማር ምዘና ዘርፍ ሀላፊ አቶ ኢሳያስ እንድረያስ የለውጡ መንግስት የትምህርት ስብራትን ለመጠገን ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
የእውቀትና ለሀገር ብልጽግና መሰረት የሆነው ትምህርት ዋና ተዋንያን መምህራን ናቸው በማለት ጠቅሰው ሀገርቱን ከድህነት ለማውጣት የሰለጠነ የሰው ሀይል የማፍራት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ተናግረዋል።
የሙያ ፍቃድ አሰጣጥ፣ የትምህርት እርከን ጥራትና ወቅታዊነት ጠብቀው እንዲሄድ ከማድረግ አኳያም ለዘረፉ ልዩ ትኩረት ተሰጥቷል ስሉም አክለዋል።
በቀጣይም የትምህርት ስብራትን በመጠገን የትምህርት ጥራት ለማሻሻል በሚደረገው እንቅስቃሴ መምህራን ተግተው መስራት እንዳለባቸው አቶ ኢሳያስ አሳስበዋል።
የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጴጥሮስ ወልደማርያም በበኩላቸው ትምህርት ለሁሉም ነገር መሰረት በመሆኑ የትምህርት ጥራት ችግር ለማሻሻል በርካታ የሪፎርም ስራዎች መሰራቱን ጠቁመዋል።
ለመምህራንና ተማሪዎች ምቹ የመማሪያ አከባቢ ለመፍጠርም ከባለድርሻዎች ጋር በመቀናጀት
በርካታ ተግባራት በመከናወን ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
በለውጡ መንግስት በትምህርት ዘርፍ የተገኙ ስኬቶች በማጉላትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በማረም የትምህርቱን ዘርፍ ለማበልፀግ በጋራ መስራት አለብን ብለዋል።
የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት፣አሳታፊነትና አካታችነት እንዲሁም የግብዓት አቅርቦትና የመምህራን ደረጃ ማሻሻል ሥራ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የወላይታ ዞን ትምህርት መምሪያ ሀላፊ አቶ ሚካኤል ሳኦል ተናግረዋል።
ሀገር መበልጸግ የሚችለው በትምህርት በመሆኑ የሰለጠነ የሰው ሀይል በማፍራት አኳያ መምህራን የበኩላቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል።
ለተማሪዎች የትምህርት ግብአት ከማቅረብ ጀምሮ መምህራን የትምህርት ደረጃቸውን እንዲያሻሽሉ አጫጭር ስልጠናዎች ከመስጠት አኳያው በትኩረት እየሰራ ይገኛልም ስሉ ተናግረዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲያስቀጥል በጋራ እንደሚሰሩ ጠቅሰው በትምህርት ተቋማት የሚስተዋሉ ጉድለቶችንና መምህራን የሚያነሷቸውን ችግሮች መንግስት ትኩረት ሰጥቶ አቅዶ መፍታት እንዳለበትም ጠይቀዋል።
አዘጋጅ፡- በቀለች ጌቾ ከዋካ ጣቢያችን
More Stories
በሀሳብ ልዕልና የሚያምን የፖለቲካ ሥነ-ምህዳርን በማስፋት ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በመመካከርና በመደጋገፍ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ መቆርቆር ቀበሌ ያስገነባው የንጹህ መጠ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
የኡዱሂያ የዕርድ ስርዓት….የአብሮነት ነፀብራቅ