በሸካ ዞን የሚገኙ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ባለድርሻ አካላት “የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና ለሁለንተናዊ ብልፅግና” በሚል መሪ ቃል በማሻ ከተማ ውይይት አካሂዱ
በሀገራችን ባለፉት የለውጥ ዓመታት በፖለቲካው፣ በኢኮኖሚና በማህበራዊ ዘርፍ የተመዘገቡ ስኬቶች በሚዲያና ኮሙኒኬሽን በማስተዋወቅ መላው ህዝብ የልማት ተነሳሽነቱን እንዲያሳድግ ማድረጉን በመድረኩ ላይ የተገኙት የሸካ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አበበ ማሞ ጠቁሟል።
በዞኑ ያሉ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን መዋቅሮች እውነተኛና ሚዛናዊነቱን የጠበቀ መረጃ በማሰራጨት እንዲሁም እንደ ሀገር ታሪካዊ ገድሎችን፣ መልካም ባህላዊ እሴቶቻችን እንዲሁም የቱሪስት መስህቦችንና ፀጋዎችን በማስተዋወቅ ለሃገር ገጽታ ግንባታ መስራት እንደሚገባም ጠቁመዋል።
ሚዲያ ዘላቂ ሰላም፣ አንድነትና ብልጽግናን በማረጋገጥ ረገድ እምቅ አቅም ያለው ተቋም በመሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች ተዓማኒነት ያላቸው መረጃዎች በማሰራጨት ለሁለንተናዊ ልማትና እድገት ትኩረት ሰጥቶ መስራት እንዳለባቸውም አቶ አበበ ማሞ ጠቁመዋል ።
አሁን ለምንገኝበት ዓለምአቀፋዊ እና ሀገራዊ ሁኔታ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ሚና ከፍተኛ መሆኑን የገለፁት የሸካ ዞን መንግስት ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙሉጌታ አድራሮ በሚከሰቱ ሁኔታዎች የማይናወጥ ጠንካራ ሚዲያ በመፍጠር ውጤታማ ስራዎችን መስራት ይገባል ብለዋል።
ትክክለኛ መረጃዎችን ተደራሽ በማድረግ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት መከላከል ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ከነጠላ ትርክት ወጥተን ገዥ ትርክትን መገንባት ያስፈልጋል ያሉት አቶ ሙሉጌታ የለውጡ መንግስት ለሚዲያ ነጻነት ፈር ቀዳጅ ስራ የሰራ ቢሆንም ይህንን ነጻነት ለመልካም ስራ የተጠቀሙት የሚዲያ አካላት እንዳሉ ሁሉ ባልተገባ መንገድ ለጥፋት የሚጠቀሙ አካላትን መከላከል እንደሚገባም በውይይቱ ተጠቁሟል።
የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን በመጠቀም ለግል ጥቅማቸው የሚንቀሳቀሱ፣ ከውጭና ከውስጥ የሀገራችንን ለውጥ የማይፈልጉ አካላት እንዲሁም የእርስ በእርስ ግጭት ለመፍጠር የሚጥሩትን በጋራ ለመከላከልና ውጤታማ ለውጥ በሀገራቱ እንዲመዘገብ ከማድረግ አንፃር ከተሳታፊዎች ጋር የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።
ዘጋቢ፡- ወንድማገኝ ገሪቶ ከማሻ ጣቢያችን
More Stories
በሀሳብ ልዕልና የሚያምን የፖለቲካ ሥነ-ምህዳርን በማስፋት ሁለንተናዊ የልማት ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ በመመካከርና በመደጋገፍ መስራት እንደሚገባ ተገለጸ
የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮጀክት ከ82 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ በጉራጌ ዞን ምሁር አክሊል ወረዳ መቆርቆር ቀበሌ ያስገነባው የንጹህ መጠ ውሃ ፕሮጀክት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ሆነ
የኡዱሂያ የዕርድ ስርዓት….የአብሮነት ነፀብራቅ