ሀገር የያዘችውን የብልጽግና ጉዞ እውን ለማድረግ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና የላቀ መሆኑ ተገለጸ
በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውሰጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ዙሪያ ከሚዲያ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር በሳውላ ከተማ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የጎፋ ዞን የመንግስት ኮሙኒኬሽን ገዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ብርቱካን ብርሃኑ፤ የሚዲያው ዘርፍ ሀገራችን የለውጥ ጉዞ ከጀመረችበት ጊዜ ወዲህ ለህብረተሰቡ ተአማኒ የመረጃ ተደራሽነት ስራዎችን በመስራት የዜጎች ህይወት እንዲሻሻል እና የአገሪቱ ገጽታ በአዎንታዊ መልኩ መገንባት መቻሉን ተናግረዋል፡፡
የለውጥ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በቀጣይም ጠንካራ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ስራ መሰራት እንዳለበት አሳስበዋል።
በመምሪያው ምክትል ኃላፊ በአቶ ውብነህ ኢያሱ በሀገራችን ኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካው ዘርፍ የተመዘገቡ ለውጦች ላይ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡
የዞኑ ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ጃኬቴ ዛይሰ በመድረኩ ተገኝተው እንዳሉት፤ ተአማኒነት ያለው ወቅታዊ መረጃን ለማህበረሰቡ ከማድረስ አኳያ ሚዲያ የተጣለበትን ከፍተኛ ማህበራዊ ኃላፊነነት በአግባቡ መወጣት ይጠበቅበታል፡፡
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት በአካባቢው ያሉ የቱሪስት መስህቦችን ማስተዋወቅና የተሳሳቱ ትርክቶችን መከላከል፤ በግሉ ሚዲያ የሚስተዋሉ ችግሮችን ከመፈታት አኳያ ልዩ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፡ ስንታየሁ ሙላቱ – ከሳውላ ጣቢያችን

More Stories
በጎፋ ዞን የዑባ ደብረፀሐይ ወረዳ የብልጽግና ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ፓርቲውን በሀብት ለማጠናከር ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር በላይ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረጉ
የጓሮ አትክልትና የተለያዩ ሰብሎችን በማልማት የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ መቻላቸውን በጠምባሮ ልዩ ወረዳ የሶያሜ ቀበሌ አርሶአደሮች ተናገሩ
በከተማው በተያዘው በጀት ዓመት በ5 ወራት ውስጥ 1 ቢሊየን 5 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰብ መቻሉን የአርባምንጭ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች መምሪያ አስታወቀ