ለኢትዮጵያ ቀጣይ ጉዞ የሚዲያ ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለፀ
በኢትዮጵያ የብልጽግና ጉዞ ውስጥ የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ሚና እና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በዲላ ከተማ እየተካሄደ ነው።
የጌዴኦ ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ዜና ማሞ፤ ሚዲያዎች ከተቋቋሙለት ዓላማ አንጻር ተአማኒነት ያላቸውን መረጃዎች ለህብረተሰቡ ከማድረስ ባሻገር አካባቢን የማስተዋወቅ ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው ብለዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ምህረቱ ተፈሪ፤ በሀገር ግንባታ ረገድ ሚዲያዎች ያላቸው ሚና ቀላል የማይባል እንደሆነ ገልፀው ሁሉም ሃላፊነታቸውን በሚገባ እንዲወጡ አሳስበዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ኃላፊዎችና ባለሙያዎች እንዲሁም የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ዘጋቢ: ለምለም ኦርሳ – ከይርጋጨፌ ጣቢያችን

More Stories
ባለፉት አመታት የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ስርአትን በማዘመን የተሰሩ ስራዎች አርሶ አደሩን ተጠቃሚ ማድረጋቸውን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ የመሬት አስተዳደርና አጠቃቀም ኤጀንሲ አስታወቀ
የጤናው ዘርፍ ተግባራት በኃላፊነት እና በቅንጅት ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ
በኮንታ ዞን የሽግግር ም/ቤት 4ኛ ዙር 4ኛ ሥራ ዘመን 26ኛው መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ